ኦቪድ ሪል እሰቴት፣ ራይድ ትራንሰፖርት (Hybrid Designs PLC) እና ሰዋሰው መልቲሚዲያ በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን የስራ ውል ስምምነት በዛሬው እለት ተፈራርመዋል።
በፊርማ ስነስርዓቱ ላይ እንደተገለጸው ራይድ ትራንስፖርት ኦቪድ ሪል እስቴት በገላን ጎራ ከተማ በሚያስገነባው ዘመናዊ የራይድ መንደር ቤተሰቦቹ ተጠቃሚ የሚሆኑበትን አሰራር ለማመቻቸት ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር ሲሰራ ቆይቷል።
የሰምምነቱ አጠቃላይ ዓላማ ኦቪድ ሪል እሰቴት በHybrid Designs PLC ስር ለሚገኙ ተቋማት፣ የራይድ ቤተሰቦች የመኖሪያ ቤት ሽያጭ የዋጋ ቅናሽ አሰራርን በማመቻቸት የቤት ባለቤት ለመድረግና በአጠቃላይ የራይድ ቪሌጅ (RIDE VILLAGE) ለመገንባት ሲሆን ሀይብሪድ እና በሰሩ ያሉ ተቋማታም የራይድ ቤተሰቦችን ተጠቃሚ በሚያደርግ መልኩ ኦቪድ ሪል እስቴት ለሚያቀርባቸው የመኖሪያ ቤት ሽያጭ አገልግሎቶች የገበያ እንቅሰቃሴዎችን በማከናወን የማስተዋወቅ ስራዎችን ከሌሎች እህት ተቋማቱ ጋር በጋራ በትስስር ለመስራት ተሰማመተዋል፡፡
እንዲሁም ኦቪድ ሪል እስቴት ለራይድ ትራንስፖርት፣ በስሩ ለሚገኙ ተቋማት እና ራይድ ቤተሰብ ዘመናዊ የመኖሪያ ቤቶችን በተመጣጣኝ የዋጋ ቅናሽ ለሸያጭ የሚያቀርብ ሲሆን በአጠቃላይ OVID GELANGURA CITY RIDE VILLAGE (በኦቪድ ገላን ጉራ ከተማ የራይድ መንደር) ለመገንባት ተሰማምቷል፡፡
ሌላው ስምምነቱ የሚያካትተው በሰዋሰው መልቲ ሚዲያ በኩል የሚገኙ አንጋፋና ወጣት የጥበብ ባለሙያዎች፣ እርቲሰቶች፣ ዲጄዎች እና ከያኒያንን በተመጣጣኝ ዋጋ እና በልዩ ሁኔታ የመኖሪያ ቤት ቅናሽ ዕድል ተጠቃሚ የሚሆኑበት የተመቻቸላቸው ሲሆን ባለሙያዎቹም ኦቪድ ሪል እስቴት የሚያቀርባቸውን የቤት ሸያጭ ከአጋሮቹ ጋር ያከናውናል፡፡
ኦቪድ ሪል እሰቴት በአሁን ሰዓት የጫካ የቤቶች ፕሮጀክት፣ የኪንግሰ ታወር ፕሮጀክትን እንዲሁም የኦቪድ ገላን ጉራ ከተማ ፕሮጀክትን ይዞ እየሰራ የሚገኝ ሲሆን በኦቪድ ገላን ጉራ ከተማ ፕሮጀክት ትምህርት ቤቶች፣ የጤና ተቋማት፣ የስፖርት ማዘውተሪያዎች እና የገቢያ ማዕከሎችን የያዘ ከ60,000 በላይ መኖሪያ ቤቶች ያሉት የማህበረሰቡን የመግዛት አቅም ያገናዘበ ዘመናዊ ከተማ በመገንባት ላይ ይገኛል።
ምንጭ፡ ድሬቲዩብ


















