• BetBegara.com
  • Buy
  • Rent
  • Sale
  • Services
  • Contact Us
Betegna - ቤተኛ | Ethiopian Housing and Real Estate News & Insights
Advertisement
  • Home
  • Guides
    • Buying Guide
    • Renting Guide
    • Selling Guide
    • Knowledge Base
  • Mortgage
  • Technology
  • Legal
    • Proclamations (አዋጅ)
    • Regulations (ደንብ)
    • Directives (መመሪያዎች)
    • Community Complaints
    • Corruption (ሙስና)
  • Tender
    • Auction (ሐራጅ)
    • Land Lease (የመሬት ሊዝ)
    • Request for EOI
  • Project Highlight
  • More
    • Community & CSR
    • Construction & Projects
    • Construction Material Supply
    • Design & Innovation
    • Public Housing
    • Insights & Profiles
    • Sales & Marketing
    • Property Handover
    • Global
    • Contact Us
No Result
View All Result
Sell, Buy, Rent
  • Home
  • Guides
    • Buying Guide
    • Renting Guide
    • Selling Guide
    • Knowledge Base
  • Mortgage
  • Technology
  • Legal
    • Proclamations (አዋጅ)
    • Regulations (ደንብ)
    • Directives (መመሪያዎች)
    • Community Complaints
    • Corruption (ሙስና)
  • Tender
    • Auction (ሐራጅ)
    • Land Lease (የመሬት ሊዝ)
    • Request for EOI
  • Project Highlight
  • More
    • Community & CSR
    • Construction & Projects
    • Construction Material Supply
    • Design & Innovation
    • Public Housing
    • Insights & Profiles
    • Sales & Marketing
    • Property Handover
    • Global
    • Contact Us
No Result
View All Result
Betegna - ቤተኛ | Ethiopian Housing and Real Estate News & Insights
No Result
View All Result

የሞርጌጅ ሪፋይናንስ ኩባንያ ምስረታ በሪል እስቴት ዘርፉ የሚፈጥራቸው ለውጦች

Desalegn Kebede by Desalegn Kebede
September 5, 2026
in Insights & Profiles, Mortgages & Finance
A A
0
0
SHARES
Share on FacebookShare on LinkedIn

በሀገራችን የመጀመሪያው የሞርጌጅ ሪፋይናንስ ኩባንያ መንግስት 100 ቢሊዮን ብር ካፒታል በማስቀመጥ እና የአለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) 200 ሚሊዮን ዶላር በማበርከትብለማቋቋም መታሰቡን በዚህ ሳምንት መስማታችን ለሀገራችን የሪል እስቴት ዘርፍ ትልቅ ዕድል ነው።

በሪል እስቴት ኢንቨትመንት ውስጥ ካሉት ዋና ዋና ባለድርሻ አካላት መካከል መንግስት ፣ የካፒታል ማርኬት ( ገንዘብ አቅራቢ)፣ አልሚ፣ ቤት ገዢና ባለሙያዎች ይገኙበታል።

ወደ ሀገራችን የሪል እስቴት ዘርፍ ውስጥ በምንገባበት ወቅት ወቅታዊ በተመጣጣኝ ዋጋ የሚቀርብ የቤት አቅርቦትን ለማስካት ያልተቻለው በሁሉም (አምስቱም) ባለድርሻ አካላት ምክንያት ነው ብሎ መውሰድ ይቻላል።

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በመንግስት በኩል እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎች በዘርፉ ውስጥ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት በተሻለ መጠን እየተወጣ መሆኑን አመላካች ነው። ለዚህም የመሬት አቅርቦት መሻሻል፣ የሪል እስቴት አዋጅ መጽደቅ (ስራ ላይ ባይውልም)፣ የውጭ ዜጎች ቤት እንዲገዙ የሚያችል አዋጅ ማጽደቁ፣ በአብሮ ማልማት ከባለ ሀብቴች ጋር አብሮ መስራቱ፣ የተለያዩ የቤት ግንባታ ፕሮግራሞችን መጀመሩ….መጥቀስ ይቻላል።

አሁን ሊመሰረት በእንቅስቃሴ ላይ ያለው የሞርጌጅ ሪፋይናንሲንግ ኩባንያ ምስረታም አንዱ ማሳያ ተደርጎ የሚወሰድ ነው። ይህ የሪፋይናንሲንግ ተቋም ባንኮች የረጅም ጊዜ ሞርጌጅ ብድር ለመስጠት ያለባቸውን የአቅም ውሱንነት መፍትሄ በመስጠት የረጅም ጊዜ ብድር እንዲሰጡ የሚያስችል ገንዘብ ያቀርባል ይህም ባንኮች በሪል እስቴት ዘርፍ ውስጥ አዳዲስ ብድሮችን እንዲሰጡ ያስችላቸዋል።

ይህም በዘርፉ ውስጥ ያለው ገንብቶ ለመሸጥ ከመቸገር ጋር ያለውን Liquidity Risk ያቃልላል፣ በርካታ ቤቶች እንዲገነቡ ያበረታታል፣ የገንዘብ አቅርቦት ሲሻሻል ከፍተኛ የሆነው የብድር ወለድ ይቀንሳል፣ ቤት ገዢዎች የተራዘመ የብድር መክፈያ ጊዜ ስለሚመቻችላቸው በየጊዜው የሚከፍሉት የብድር መመለሻ ገንዘን መጠን ይቀንስላቸዋል፣ በርካታ ብቃት ያላቸው አልሚዎች ወደ ዘርፉ እንዲቀላቀሉ ያነሳሳል፣ የውጭ ባለሀብቶችን ወደ በዘርፉ በመማብ ቀጥተኛ የሆነ የሚየውጭ ምንዛሪ ግኝት (FDI) ያሳድጋል ……

በተጨማሪም በሪፋይናንስ ብቁ ለመሆን የቤት መግዣና መገንቢያ ብድር አቅራቢዎች (ሞርጌጆች ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና IFC መስፈርቶችን ማሟላት ስላለባቸው ለብድር ብቁ ለመሆን አልሚዎች ወደ ትክክለኛ የመሬት ሰነድ እና የግንባታ ጥራት እንዲሄዱ ይገፋፋቸዋል። ይህም በዘርፉ ያለውን አለመተማመን ይቀንሳል።

ነገር ግን የሪል እስቴት ዘርፍ መሬት ስለቀረበ፣ የመገንቢያና የመግዣ ስለተመቻቸ ዘርፉ ስኬቱ ሙሉ አያደርገውም። ለቅኬታማነቱ የሚከተሉት እንደ ተግዳሮት ሊታዩ ይችላሉ:-

  1. የመሬት ሰነድ እና የህግ ችግሮች፦ የሪፋይናንስ ኩባንያ ግልጽ የመሬት ሰነድ ለሌላቸው ንብረቶች ሞርጌጅ መግዛት አይችልም። የመሬት ምዝገባ ስርዓት መዘግየት ለአልሚዎች ትልቅ እንቅፋት ሆኖ ይቀራል።
  2. የግንባታ ወጪ፦ ፋይናንስ ቢሻሻልም፣ ከውጭ የሚገቡ ብረት እና ማሽኖች ዋጋ በሎጂስቲክስ እና በውጭ ምንዛሬ እጥረት ምክንያት ከፍተኛ ሆኖ ይቀራል፣ ይህም የቤት ዋጋን ከፍ ያደርገዋል።
  3. የብቁነት መስፈርት፦ አልሚዎች በIFC የሚደገፈውን የቴክኒክ እና የአካባቢ ጥበቃ ጥብቅ መስፈርቶች ለማሟላት ሊቸገሩ ይችላሉ፣ በተለይም አነስተኛ የሀገር ውስጥ አልሚዎች ተጠቃሚ ለመሆን ይቸገራሉ።
  4. የመግዛት አቅም ገደብ፦ ከቤት ገዢዎች የሚጠበቀውን የረጅም ጊዜ ወርሃዊ ክፍያን ይቀንሳል፣ ነገር ግን አጠቃላይ የቤቱ ዋጋ (ዋና ገንዘብ + ወለድ) በእጅጉ ይጨምራል። ገዢዎች ይህንን ተረድተው ካልተዘጋጁ የገዢ ችግር ሊፈታ አይችልም።
  5. የቅድመ ክፍያ እንቅፋት፦ አብዛኛዎቹ ሞርጌጆች 20-30% የቅድመ ክፍያ ይጠይቃሉ። ለአማካይ የኢትዮጵያ ቤተሰብ ይህን መጠን መቆጠብ ትልቅ ተግዳሮት ነው።
  6. የገቢ ማረጋገጫ፦ መደበኛ የባንክ ዘርፍ የተረጋገጠ ገቢ ማረጋገጫ ይፈልጋል። ከፍተኛ የሆነው የኢትዮጵያ የስራ ኃይል ክፍል መደበኛ ባልሆነ ዘርፍ ውስጥ ስለሚገኝ፣ ለአዲሱ ብድር ብቁ ላይሆኑ ይችላሉ።
  7. የቤት መወረስ አደጋ፦ ረጅም የብድር ጊዜ ማለት ገዢዎች ለረጅም ጊዜ የተረጋገጠ አስተማማኝ ገቢን ይፈልጋል። ነገር የአገራችን ኡኮኖሚ ለመገመት ከሚከብድ የዋጋ ንረትና ለአንዳንድ ጊዜም ለስራ ማጣት የተጋለጡ ናቸው፣ ይህም ንብረታቸውን የማጣት ስጋት ሊያስከትል ይችላል።

ስለዚህ ይህ ጥሩ አጋጣሚ ወደ ዜጋ ጥቅም እንዲቀየር የሚከተሉት ትኩረት ቢዱረግባቸው መልካም ነው:-

፩)በመንግስት በኩል

  1. የዲጂታል መሬት ምዝገባ ማፋጠን፦ የተቋሙ ስኬት ግልጽ ሰነድ ላይ የተመሰረተ ነው።እየተከናወነ ያለውን የከተማ መሬት ምዝገባዎችን በዲጂታል ማፋጠን ለባንኮች አስፈላጊ ሰነዶችን በፍጥነት ማቅረብ።
  2. የተናጠል ካርታ አሰጣጥን ማፋጠን:- ከባንክ ብድር ጋር የተያያዙ ቤቶች ግብይት አንዱ ዋና ችግር በሚፈለገው መስፈርት መሰረት የግንባታው ዕርክፕን ለደረሰ ፕሮጀክት ተናጠል ካርታ ለመስጠት ያለው መዘግየት ነው።
  3. የፋይናንስ ትምህርት ማካሄድ፦ ለሪል እስቴት ግብይት ባለሙያዎችና ቤት ገዢዎች ስለ ረጅም ጊዜ ዕዳ አስተዳደር፣ የወለድ ስሌት እና የቤት ባለቤትነት ሃላፊነት ማስተማር ። ይህም ግብይቱ በዕውቀት ላይ የተመሰረተ የወደፊት የዕዳ አለመክፈልንም የሚቀንስ ይሆናል።
  4. የውጭ ምንዛሬ ቅድሚያ ቢመቻች፦ ለገንቢዎችና የግንባታ ቁሳቁስ አስመጪዎችና አምራቾች ተደራሽ የሆነ የውጭ ምንዛሬ እንዲያገኙ መደረግ አለበት፤ አለበለዚያ “ተመጣጣኝ” የሚባል ዋጋ ስለማይኖር በአቅርቦት ወጪ ንረት ይሸረሸራል።

፪) የሪል እስቴት አልሚዎች፦

  1. በዲዛይን ደረጃ ካሉ ይልቅ የተገነቡ ቤቶችን ለገበያ ቢያቀርቡ ፦ ለግንባታ የሚሆን ብድር እስካገኙ ድረስ በዕቅድ ላይ ካሉ የ3D ህንጻ ይልቅ፣ የተጠናቀቁ ቤቶችን በመሸጥ ላይ ሊያተኩሩ ይገባል።የቢዝነስ ሞዴላቸው ሊቀየር ይገባል።
  2. ወጪ ቆጣቢ ፕሬጀክቶችን መተግበር፦ የሚገነቧቸው ቤቶች ተበድሮ ገዢዎችን ለማስቻል ፕሮጀክቶቻቸውን ከውጭ ወደ ሀገር ውስጥ ከሚገቡ ቁሳቁሶች ጥገኝነት በመቀነስ እና ዋጋን ለመቆጣጠር ፣ ዘመናዊ የግንባታ ቴክኒኮችን እና የሀገር ውስጥ ቁሳቁሶችን ቢጠቀሙ።
  3. ቀድመው ከባንኮች ጋር መስራት፦ ፕሮጀክቶቻቸው ለሪፋይናንስ ብቁ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ከአበዳሪ ባንኮች ጋር ቀድመው ይስሩ፣ የ የሚገነቧቸው ቤቶች “ለሞርጌጅ ዝግጁ” እንዲሆኑ ያደርጋል።

፫) ለቤት ገዢዎች፦

  1. ለቅድመ ክፍያ ይዘጋጁ፦ 20-30% የሚሆነውን የቅድመ ክፍያ ለማሰባሰብ በተለይ መቆጠብ ይጀምሩ።
  2. ገቢያቸውን መደበኛ ያድርጉ፦ የሀገራችን የግለሰብ ገቢ ግራ አጋቢ ነው። ጥቂት ሰው በወር ከሚከፈለው ገቢ በተጨማሪ ተጨማሪ ስራ በመስራት፣መደበኛ ያልሆኑ ስራዌችን በመስራት፣ ከውጭ ዘመድ በሚላክ ድጎማ ራሱን የሚያስተዳድር ስለሆነ ለአበዳሪ ባንኮች እውነተኛ ገቢውን አሳውቆ ለቤት መግዣ ብድር ብቁ ለመሆን ይቸገራል። በመሆኑም ሁሉንም ገቢዎችና የንግድ ግብይቶች በመዘገብ እና ግብርም በመክፈል የገቢ ታሪክ ቢገነቡ መልካም ነው።
  3. በባንኮች የሚቀርቡ የብድር ውሎችን ያወዳድሩ፦ የሪፋይናንስ ስርዓት እያደገ ሲሄድ፣ የተለያዩ ባንኮች የተለያዩ የወለድ ተመኖች ይሰጣሉ። ቤት ገዢዎችም የተሻለውን አመታዊ የወለድ ተመን (APR) ለማግኘት የባንክ ውሎችን ይመርምሩ ያወዳድሩ።
  4. አጠቃላይ ወጪን ይረዱ፦ ወርሃዊ ክፍያውን ብቻ ሳይሆን በ15 -20 ዓመት ውስጥ ሙሉ በሙሉ የሚከፍሉትን አጠቃላይ ገንዘብ አስሉ። ይህ ቤቱ በረጅም ጊዜ በእውነት ተመጣጣኝ መሆኑን ለማወቅ ይረዳል።

ስናጠቃልለው ይህ አዲስ ተቋም ለሀገራችን የቤቶች ገበያ ትልቅ እድል ነው። ነገር ግን ስኬቱ የሚወሰነው መንግስት፣ ባንኮች፣ አልሚዎች እና ገዢዎች በትብብር መስራታቸው ላይ ነው። ጥንቃቄ የተሞላበት እቅድ እና ትክክለኛ መረጃ ይህን ፕሮግራም ለሁሉም የሚጠቅም ማድረግ ይችላል።

Tags: mortgages
Previous Post

ካቮድ ኮሜርሻል በአዲስ ዓመት ዋዜማ ለደንበኞቹ የመኪና እና የቤት ዕቃዎችን ያካተተ ታላቅ የዕጣ ሽልማት አበረከተ

Next Post

አማን ፕሮፐርቲስ እስከ 30% ቅናሽ ያደረገበት “አማን አዲስ ኤክስፖ” በደማቅ ሁኔታ ተከፈተ

Desalegn Kebede

Desalegn Kebede

ኢንጂነር ደሳለኝ ከበደ የሲቪል ምህንድስና ባለሙያ፣ የሪል እስቴት አማካሪ፣ አሰልጣኝ እና ጸሐፊ ሲሆኑ፤ በግንባታ፣ በሪል እስቴት ስልጠና እና በገበያ ጥናት ዘርፎች የሚታወቀውን አቡቀለምሲስ ግሩፕ (Abukelemsis Group) መሥራችና ዋና ሥራ አስኪያጅ ናቸው።

ተዛማጅ ጽሑፎች

የሪል እስቴት አልሚዎች ማህበር የ7% የብድር ወለድ ጥያቄ በባለሙያዎች መካከል ያስነሳው ክርክር
Insights & Profiles

የሪል እስቴት አልሚዎች ማህበር የ7% የብድር ወለድ ጥያቄ በባለሙያዎች መካከል ያስነሳው ክርክር

November 18, 2026
በከፊል የተጠናቀቁ አፓርትመንቶች መኖሪያ ቤቶች አይደሉም
Insights & Profiles

በከፊል የተጠናቀቁ አፓርትመንቶች መኖሪያ ቤቶች አይደሉም

September 25, 2026
ተሾመ ግርማ በቴምር ፕሮፐርቲስ የሽያጭና ማርኬቲንግ ሥራ አስኪያጅ፤ ቀደም ሲል የሀሞና መስራችና በአያት ሪል እስቴት የሽያጭ ሰራተኛ
Insights & Profiles

በስምንት ዓመታት የሪል እስቴት ጉዞዬ ከ1,000 በላይ ቤቶችን ለመሸጥ የቻልኩበት ሚስጥር

September 25, 2026
Next Post
አማን ፕሮፐርቲስ እስከ 30% ቅናሽ "አማን አዲስ ኤክስፖ" በደማቅ ሁኔታ ተከፈተ

አማን ፕሮፐርቲስ እስከ 30% ቅናሽ ያደረገበት "አማን አዲስ ኤክስፖ" በደማቅ ሁኔታ ተከፈተ

  • Trending
  • Comments
  • Latest
የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ 721/2004

የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ 721/2004

April 23, 2024
ስለ ግብር የሚከፈልበት የቤት ኪራይ ገቢ

ስለ ግብር የሚከፈልበት የቤት ኪራይ ገቢ

April 6, 2024
በአዲስ አበባ የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን ላይ በድጋሚ ማሻሻያ ተደረገ

በአዲስ አበባ የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን ላይ በድጋሚ ማሻሻያ ተደረገ

April 3, 2024
የመሬት ልማትና አስተዳር ደንብ ቁጥር 163/2016

የመሬት ልማትና አስተዳር ደንብ ቁጥር 163/2016

April 22, 2024
ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

August 18, 2023
Home pic

ቤት ለሚገዙ እና ለሚሸጡ አካላት ማሳሰቢያ ተሰጠ

0
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤት አቅርቦትን ለማሳደግ የሚያስችል ውይይት ከሪል እስቴት አልሚዎች ጋር ውይይት አደረገ!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤት አቅርቦትን ለማሳደግ የሚያስችል ውይይት ከሪል እስቴት አልሚዎች ጋር ውይይት አደረገ!

0
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ያስተዋወቀበትን የገርጂ መኖሪያ መንደር ፕሮጀክት ሊያስመርቅ ነው

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ያስተዋወቀበትን የገርጂ መኖሪያ መንደር ፕሮጀክት ሊያስመርቅ ነው

0
ባለ 9 ወለል ህንፃ በተጀመረ በ69ኛ ቀኑ ተጠናቀቀ!!

ባለ 9 ወለል ህንፃ በተጀመረ በ69ኛ ቀኑ ተጠናቀቀ!!

0
ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

0
የሪል እስቴት አልሚዎች ማህበር የ7% የብድር ወለድ ጥያቄ በባለሙያዎች መካከል ያስነሳው ክርክር

የሪል እስቴት አልሚዎች ማህበር የ7% የብድር ወለድ ጥያቄ በባለሙያዎች መካከል ያስነሳው ክርክር

November 18, 2026
በጋዜቦ አደባባይ አካባቢ በግንባታ ሂደት ላይ ከነበረ ሕንጻ ላይ የወደቁ ሦስት ሠራተኞች ሕይወታቸውን አጡ

በጋዜቦ አደባባይ አካባቢ በግንባታ ሂደት ላይ ከነበረ ሕንጻ ላይ የወደቁ ሦስት ሠራተኞች ሕይወታቸውን አጡ

November 14, 2026
በ5 ዓመታት ቤቶችን ገንብተን ለማስረከብ የገባነውን ቃል በተግባር ለማረጋገጥ እየተጋን ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

በ5 ዓመታት ቤቶችን ገንብተን ለማስረከብ የገባነውን ቃል በተግባር ለማረጋገጥ እየተጋን ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 13, 2026
የ1.5 ሚሊዮን መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ወደ ተግባር ምዕራፍ ተሸጋግሯል

የ1.5 ሚሊዮን መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ወደ ተግባር ምዕራፍ ተሸጋግሯል

November 12, 2026
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከዩኤን ሃቢታት ዋና ዳይሬክተር አናክላውዲያ ሮስባክ ጋር መወያየታቸውን ገለፁ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከዩኤን ሃቢታት ዋና ዳይሬክተር አናክላውዲያ ሮስባክ ጋር መወያየታቸውን ገለፁ

November 11, 2026

ብዙ የተነበቡ

  • የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ 721/2004

    የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ 721/2004

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ስለ ግብር የሚከፈልበት የቤት ኪራይ ገቢ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአዲስ አበባ የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን ላይ በድጋሚ ማሻሻያ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የመሬት ልማትና አስተዳር ደንብ ቁጥር 163/2016

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Categories

  • Community & CSR (28)
  • Construction & Projects (29)
  • Construction Material Supply (9)
  • Design & Innovation (18)
    • Architecture (2)
    • Technology (14)
  • Global (4)
  • Insights & Profiles (20)
  • Legal Updates (89)
    • Community Complaints (8)
    • Corruption (ሙስና) (2)
    • Directives (መመሪያዎች) (1)
    • Proclamations (አዋጅ) (7)
    • Regulations (ደንብ) (2)
  • Mortgages & Finance (14)
  • Property Handover (16)
  • Public Housing (71)
  • Real Estate Guides (13)
    • Buying Guide (3)
    • Knowledge Base (1)
    • Renting Guide (2)
    • Selling Guide (7)
  • Sales & Marketing (67)
  • Tenders & Bids (60)
    • Land Lease (29)
    • Request for EOI (1)
  • Home
  • Guides
  • Mortgage
  • Highlights
  • Legal Updates
  • Tenders & Bids
Betegna Logo Footer

Betegna – ቤተኛ, powered by Betbegara.com, is a media platform that focuses on Ethiopian housing and real estate news, developments, technology, policies, and lifestyle.

© 2026 Betegna – ቤተኛ | Ethiopian Housing and Real Estate News & Insights

  • Home
  • Guides
    • Buying Guide
    • Renting Guide
    • Selling Guide
    • Knowledge Base
  • Mortgage
  • Technology
  • Legal
    • Proclamations (አዋጅ)
    • Regulations (ደንብ)
    • Directives (መመሪያዎች)
    • Community Complaints
    • Corruption (ሙስና)
  • Tender
    • Auction (ሐራጅ)
    • Land Lease (የመሬት ሊዝ)
    • Request for EOI
  • Project Highlight
  • More
    • Community & CSR
    • Construction & Projects
    • Construction Material Supply
    • Design & Innovation
    • Public Housing
    • Insights & Profiles
    • Sales & Marketing
    • Property Handover
    • Global
    • Contact Us
No Result
View All Result
Sell, Buy, Rent