አማን ፕሮፐርቲስ በመካከለኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎችን ታሳቢ ያደረገ እና ከ15 እስከ 30 በመቶ የሚደርስ ቅናሽ የተደረገባቸውን 250 ቤቶች ለሽያጭ ያቀረበበት “አማን አዲስ ኤክስፖ” በላፍቶ ሞል በድምቀት ተከፈተ።
ነሐሴ 29 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ የተከፈተው ይህ ኤክስፖ እስከ ጳጉሜ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ ሲሆን፣ በቅናሽ ዋጋ ለሽያጭ የቀረቡት ቤቶች በተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች የሚገነቡ እንደሆኑ ተጠቅሷል።

አማን ፕሮፐርቲስ በሪል እስቴትና በግንባታ ዘርፍ ከ5 ዓመታት በላይ ልምድ ያላቸውን ላፍቶ ላይፍ፣ ኒው ላይፍ እና ስካይ ቪው ሪል እስቴቶችን በስሩ በማጠቃለል በአዲስ የብራንድ ስም ወደ ሥራ መግባቱን አሳውቋል። ተቋሙ እስካሁን ባለው እንቅስቃሴ ከ300 በላይ ቤቶችን ገንብቶ የሸጠ ሲሆን፣ በ2019 ዓ.ም በርካታ አዳዲስ ፕሮጀክቶችን ወደ ተግባር ለማስገባት አስፈላጊውን የቅድመ ዝግጅት ሥራ ማጠናቀቁንም ገልጿል።
በኢትዮጵያ የንግድ፣ ማኑፋክቸሪንግ እና ቴክኖሎጂ ዘርፎች ውስጥ ላለፉት 10 ዓመታት ሲንቀሳቀስ የቆየው የአማኔት ግሩፕ አካል የሆነው አማን ፕሮፐርቲስ፣ ግንባታዎቹን በራሱ የኮንስትራክሽን ድርጅት የሚያከናውን በመሆኑ በዘርፉ በስፋት የሚታየውን የፕሮጀክቶች መጓተት እና የጊዜ መራዘም ችግር እንደሚያስቀር ተገልጿል።
ምንጭ:-Fast Mereja
















