በሀገራችን የሚገኙ ባንኮች ከያዝነው የፈረንጆቹ አዲስ ዓመት ጀምሮ ቀድሞ በተወሰዱና አዲስ በሚወሰዱ ብድሮች ላይ ያለው የብድር ወለድ ምጣኔ ላይ ከነባሩ ብድር ወለድ ምጣኔ ላይ ከ 3-5% እንደሚጨምሩ ተሰምቷል።
ይህ በሪል እስቴት ዘርፍ ውስጥ በብድር ለሚያለሙ፣ ቤት ለሚገዙና ገዝተው በመክፈል ላይ ላሉ ከባድ ያልታሰበ ጫናን የሚፈጥር ነው።
ከአንድ ዓመት በፊት በነበረ ክስተት ላይ 2% የወለድ ጭማሪ ለቤት ግዢ ወይም ግንባታ ብድር የወሰደ ሰው ላይ የሚደርሰውን ተጽዕኖ በዚህ ማህበራዊ ሚዲያ በቁጥር ለማሳየት ሞክሬ ነበረ ።
በስሌቱ መሰረት በ1% የወለድ ጭማሪ እንደ ብድር መመለሻ ጊዜው የሚለካ ሆኖ እስከ 10% የሚሆን የክፍያ ጭማሪ ሊያስከትል እንደሚችል አይተን ነበር። በዚህ መሰረት ከ3-5% የወለድ ጭማሪ የሚፈጥረውን ጫና ማሰብ ቀላል ነው።
ከዓመት በፊት ተበድረው 2% የወለድ ጭማሪ የጎበኛቸው የአሁኑን ጨምሮ ከ 5-7% የብድር ወለድ ጭማሪ የጎበኛችው የጭንቅ አማላጇ ትሁናችው።
እንግዳውስ ምን እንላለን ? ቤት በብድር የገዛችሁ ረዚቁ ዱላውን መቻያ አስተማማኝ ርዝቁን ያድላችሁ። በብድር የመግዛት ዕድሉ ያላችሁ ቆም ብላችሁ አስልታችሁ ባለሙያ አማክራችሁ ግቡበት።
በነገራችን መጨረሻ በቀጣይ በአሜሪካን ሀገር ሪል እስቴት ዘርፉ ላይ ሹቀት ያመጣል ተብሎ እየተፈራ ያለው ይኽው የብድር የወለድ ጭማሪ ነው።
በሪል እስቴት ኢንቨስትመንት አስተዳደርና ግብይት መጸሃፍ ላይ ተገልጾ እንደሚገኘው በሪል እስቴት ኢንቨስትመንት ውስጥ የኢንቨስትመንት ስጋት ከሚባሉት አበይት ጉዳዮች መካከል የወለድ ምጣኔ ጭማሪ(interest rate risk) አንዱ ነው።
ማስተካከያ እንደሚደረግለት የተነገረው የገንዘብ ፖሊሲን ተከትሎ በባንኮች ላይ በብሄራዊ ብንክ የሚደረገው ከ16% ወደ 18% የሚደረገው የወለድ ጭማሪ ወደ ተበዳሪዎችም መውረዱ የሚጠበቅ ነውና በሪል እስቴት ግብይት ውስጥ የሚኖረው ተጽእኖ ምን ይመስላል? የሚለውን ለማስረዳት ይህንን ጽሁፍ አዘጋጀነ።
የ 2% የወለድ ምጣኔ ጭማሪ በቤት ገዢዎችና በተበድሮ ገንቢዎች ላክ የሚኖረው ተጽዕኖ እና ያልታሰበ ጫና ከፍ ያለ ነው። በዘርፉ ላይም መመሰቃቀልን የሚፈጥር በተቀዛቀዘው የግብይት ሂደት ላይ ተጨማሪ በረዶ እንደመቸለስ ነው።
2% የወለድ ጭማሪ ለሰሚው አነስተኛ ቢመስልም በጠቅላላው የቤት ግብይት ዋጋ ላይ የሚያደርሰው ጭማሪ ከሃያ በመቶ በላይ ነው የሚሆነው።
ለዚህ ማሳያ አንድ የ20ሚልየን ብር በ16% የወለድ ምጣኔ የቤት መግዣ ብድር ያለበትን ሰው ታሳቢ ብናደርግና ክፍያውን ለማጠናቀቅ 15 ዓመታት ቢጠበቅበትና የወለድ ምጣኔው ወደ 18% ቢያድግ የሚደርስበትን ጭማሪ እንመልከት:-
፩) መነሻ ብድር :- 20,000,000.00
መነሻ ወለድ ምጣኔ:- 16%
ብድር የመክፈያ ጊዜ :- 15ዓመታት
ወርሃዊ የወለድ ምጣኔ = (16%/12)= 1.3333%
ጠቅላላ የክፍያ ጊዜ (በወራት)= 15ዓመታት12 ወራት በዓመት = 180 ወራት የወር ክፍያ = ( 20,000,000(1.3333%/100))/(1-(1+(1.3333%/100))^(-180)= 266,660.00 ብር ይሆናል
፪) በአዲሱ የተጨመረ ወለድ = 16+2=18%
አዲሱ ወርሃዊ የወለድ ምጣኔ = (18%/12)=1.5%
አዲሱ ወር ክፍያ = ( 20,000,000*(1.5%/100))/(1-(1+(1.5%/100))^(-180)= 322,,095.00ብር ይሆናል
፫) የ2% የወለድ ጭማሪ ያስከተለው ጠቅላላ የዋጋ ጭማሪ በየወሩ ብር 55,435 ሲሆን ጭማሪው በመቶኛ ሲሰላ
[(322,095 – 266,660) / 266,660] * 100 ≈ 20.78% ይሆናል።
ከዚህ የምንረዳው በ16% ወለድ ለተወሰደ የቤት መግዣ ወይም መገንቢያ ብድር የ 2% የወለድ ጭማሪ የሚያስከትለው የዋጋ ጭማሪ 20.78% አካባቢ ይሆናል ማለት ነው።


















