ጊፍት ሪል እስቴት በመንግስትና የግል አጋርነት ልማት ፕሮግራም መሠረት፣ 12 ሺህ ቤቶችን ለመገንባት ስምምነት የፈረመ ሲሆን የዚህ ፕሮግራም በመጀመሪያው ዙር ሊገነባ ለታቀደው የ4 ሺህ ቤቶች ግንባታ የማስጀመር ስነ ሥርዓት የመንግሥት ከፍተኛ አመራሮች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በይፋ አካሂዷል፡፡

ከዚህ ቀደም ጊፍት ሪል እስቴት በመንግስት እና በግል አጋርነት መርሃ ግብር 4 ሺ ቤቶችን ለመገንባት ዝግጅት እያደረገ እንደሆነ መግለፃችን ይታወቃል።
በጊፍት ሪል እስቴት እና የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የጋራ መኖሪያ ቤቶችን በጋራ ለማሳካት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ
ይህ የመኖሪያ መንደር ከፍታቸው ከ14 እስከ 22 ወለል ያካተቱ 3 ሺህ 540 የመኖሪያ፣ 460 የሱቅ፣ ባጠቃላይ ከ4 ሺህ በላይ ቤቶች ሲኖሩት፣ ትምህርት ቤትና ሌሎች ማህበራዊና ማህበረሰባዊ መገልገያዎችን የሚያካትት ይሆናል፡፡

የፕሮጀክቱ ግንባታ በሶስት ዓመት ውስጥ የሚጠናቀቅ ይሆናል፡፡
የመጀመሪያው ዙር ግንባታ እንደተጋመሰ በሁለተኛ ዙር ለሚገነቡ ተጨማሪ 8 ሺህ ቤቶችና የንግድ ማዕከላት ጊፍት ሪል እስቴት ከእህት ኩባንያዎቹና ዓለም ዓቀፍና አገር አቀፍ አጋሮቹ ጋር በዲዛይን፣ ቴክኖሎጂና ፋይናንስ የቅድመ ዝግጅት ሥራ በመስራ ላይ ይገኛል፡፡
በመርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው የግንባታ ተገቢ ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቅቆ ወደ ስራ ለገባው ጊፍት ሪል እስቴት በነዋሪዎቹ ስም ምስጋና አቅርበዋል።

















