ሜሪት ፕሮፐርቲስ (Merit Properties) የመጀመሪያ ዓመት የስኬት ጉዞውን በማስመልከት የሚያካሂደውን የሁለት ወር የማስተዋወቅ ዘመቻ ለማስፈጸም ከTH Media Group ጋር የአጋርነት ስምምነት ተፈራረመ።
በፊርማ ሥነ-ሥርዓት ሁለቱ ተቋማት “One Year, One Vision, The Next Chapter” ወይም “አንድ ዓመት፣ አንድ ራዕይ፣ ቀጣዩ ምዕራፍ” በሚል መሪ ቃል በሚከናወነው የዘመቻ ሥራ ላይ በትብብር ለመስራት ተስማምተዋል።
ይህ የተደረገው የስምምነት ውል ሜሪት ፕሮፐርቲስ ባለፈው አንድ ዓመት ያስመዘገበውን ስኬት፣ የወደፊት ራዕዩን እና ቀጣዩን የሥራ ምዕራፍ ለሕዝብ በስፋት ለማስተዋወቅ የሚያግዙ የተለያዩ የሚዲያ፣ የኢቨንት እና የሕዝብ ግንኙነት (PR) ሥራዎችን በጋራ ማከናወንን ያካትታል።
በዘርፉ ከ9 ዓመታት በላይ የሚዲያና የኢቨንት ሥራዎች ልምድ ያለው TH Media Group፣ የሁለት ወሩን ዘመቻ በፈጠራ፣ በስትራቴጂ እና በተቀናጀ የሚዲያ አቀራረብ ለማስፈጸም ይሰራል።
ይህ አጋርነት የሜሪት ፕሮፐርቲስን የስኬት ጉዞ በማስታወስ ብቻ ሳይወሰን፣ የወደፊት ዕቅዶቹንና ራዕዩን ለማስተዋወቅ አዲስ የሥራ ምዕራፍ ይከፍታል ተብሏል።
















