እልልታ ሪል እስቴት አርቲስት መሰረት መብራቴን የብራንድ አምባሳደር በማድረግ በዛሬው እለት ሰኔ 14/2016 ዓም በመቄዶኒያ የበጎ አድራጎት ድርጅት በመገኘት ሾመዋል።
የመቄዶኒያ ማዕከል ጉብኝት እንዲሁም የአረጋውያን ምገባ ተከናውኗል።
የእልልታ ሪል እስቴት ተወካይ አቶ ቢረሳው ምናሉ እልልታ ከተቋቋመበት ዋና ተግባር በተጓዳኝ ማህበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣትም በከተማችን ብሎም በሀገር አቀፍ ደረጃ በርካታ የበጎ አድራጎት ስራዎች በመስራትም ይታወቃል ብለዋል። የድርጅታችን የብራንድ አምባሳደር አድርጎ ከሾማት ከተወዳጇ ሁለገብ አርቲስት መሰረት መብራቴ ጋር የአረጋውያን ጉብኝትና ምገባ እንዲሁም የፊርማ ስነ ስርዓት በማድረጉ ከፍተኛ ክብር ይሰማዋል ብለዋል፡፡

የእልልታ ሪል እስቴት የብራንድ አምባሳደር አርቲስት መሰረት መብራቴ ከአረጋዊያን ጋር ማዕድ በማጋራቷ እንዲሁም ከእልልታ ሪል እስቴት ጋር ለመስራት እድሉን በማግኘቷ የተሰማትን ክብር ገልጻለች።
ቢአኤካ ጠቅላላ ንግድ (BEAEKA GENERAL BUSINESS) እና የጀር ኃ.የተ.የግ.ማ የሆነው እልልታ ሪል እስቴት ፣ በሪል እስቴት ልማት፣ በሲሚንቶ ፍብሪካ እና በተለያዪ ፋብሪካዎች፣ በማዕድን፣ በግንባታ ዕቃዎች አምራችነት፣ በግንባታ ማሽነሪዎች እና ቁሳቁሶች አስመጪ እና የግንባታ እቃዎች የጅምላ ንግድ ላይ የተሰማራ ሀገር በቀል ድርጅት ነው።
ምንጭ፦ ፋስት መረጃ


















