አንጋፋዋ የሙዚቃ ንግስት አርቲስት አስቴር አወቀ እና ሜትሮፖሊታን ሪል እስቴት በጋራ ለመስራት Partnership for a Better Life የተሰኘ አጋርነት መፈራረማቸው ዛሬ ህዳር 19/2017 ዓ.ም ይፋ አድርጓል።
የተለያዩ አለም አቀፍ ሽልማቶችን እና የሚዲያ ሽፋኖችን በማግኘት እና የሀገሯን ሙዚቃ በድምቀት በማስተዋወቅ የምትታወቀው የሙዚቃ ንግስት አሁን ደግሞ ከሜትሮፖሊታን ሪል እስቴት ጋር በህብረት በመሆን የተለያዩ የስነ ጥበብ፣ የበጎ አድራጎት እንዲሁም የሚዲያ ስራዎችን ለህዝብ እንደምታደርስ የአስቴር አወቀ ማናጀር ወ/ሮ አዳነች ወርቁ ገልጻለች።


የሜትሮፖሊታን ሪል እስቴት የሽያጭ እና የማርኬቲንግ ዳይሬክተር አቶ አለማየሁ ተሬሳ እንደገለጹት በዚህም ስምምነት ለህዝብ መልካም ነገር የማድረስ እቅድ እንዳላቸው አሳውቀዋል።
ሜትሮፖሊታን ሪል እስቴት በአሜሪካን ሀገር ለ30 ዓመታት ቤቶችን እየገነባ ሲያስረክብ የቆየ ሲሆን በቱርክም በተመሳሳይ መልኩ በቤት ልማት ስራ ላይ መቆየቱ ተገልጿል።
በሀገራችን ኢትዮጵያ ደግሞ ከ2015 G.C ጀምሮ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ የቅንጦት አፓርታማዎችን በአዲስ አበባ ቁልፍ ቦታዎች በመገንባት ላይ ይገኛል። በዚህም መሰረት ሁለት ህንጻዎችን ገንብቶ ያስረከበ ሲሆን አምስት የሚሆኑ ደግሞ በግንባታ ደረጃ ላይ እንዳሉ ተገልጿል።


















