ኮምፓስ ፕሮፐርቲስ የ2019 አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ የማኅበራዊ ተሳትፎ ኃላፊነቱን ለመወጣት ለሴት ተማሪዎች የንጽህና መጠበቂያ (ሞዴስ) ድጋፍ አደርጓል።
ድርጅቱ ድጋፍ ያደረገው በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 ለሚገኘው የተባበሩት አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ነው።
ድጋፉም በት/ቤቱ ለሚማሩ 200 ሴት ተማሪዎች ለአንድ ዓመት የሚሆን የንጽህና መጠበቂያ (ሞዴስ) ቁሳቁስ እንደሆነም ተገልጿል።
በስጦታ ርክክብ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የኮምፓስ ፕሮፐርቲስ የገበያና ሽያጭ ክፍል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ተኩ “ኮምፓስ ፕሮፐርቲስ ቃል በገባው መሠረት በዛሬው ዕለት ድጋፉን ያደረገ ሲሆን፣ ወደፊትም ማኅበራዊ ኃላፊነቱን አጠናክሮ ይቀጥላል” ብለዋል። አክለውም ድርጅታቸው አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ ለመኖሪያና ለንግድ ቤት ገዢዎች እስከ 30 በመቶ የሚደርስ ልዩ የበዓል ቅናሽ ማዘጋጀቱን ገልጸዋል።
የወረዳ 03 ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዋኩማ ጎንፋ በበኩላቸው የተደረገውን ድጋፍ አድንቀው፣ ሌሎች ተቋማትም ተመሳሳይ ማኅበራዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።
የትምህርት ቤቱ ም/ርዕሰ መምህር እህቴነሽ ተ/ያሬድ የተደረገውን ደጋፍ በተገቢ መንገድ ለሴት ተማሪዎች እናቀርባለን ብለዋል።
ኮምፓስ ፕሮፐርቲስ በዘርፉ የካበተ ልምድ ያላቸውን ኢትዮጵያውያን እና አንቱታን ያተረፉ የቻይና ባለሙያዎችን በማጣመር፣ በጥራት እና በአጭር ጊዜ ግንባታዎችን በማጠናቀቅ በዘርፉ አዲስ መለኪያ ማስቀመጥ የቻለ ተቋም ነው።
ምንጭ፦ Fast Mereja
















