ጀንቦሮ ሪል እስቴት በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ቡልቡላ 93 ማዞሪያ አካባቢ በአንድ ዓመት ከስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ሰርቶ ያጠናቀቀውን ሦስተኛውን የሪል እስቴት ኘሮጀክት ዛሬ የካቲት 28 ቀን 2016 ዓ.ም ከፍተኛ አመራሮች፣ ባለሀብቶች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ለቤት ገዥዎቹ ቁልፍ አስረክበዋል።
ዛሬ የተመረቀው እና ለቤት ገዢዎቹ የተላለፈው ሦስተኛው ኢስት ሳይድ የመኖርያ አፓርትመንት ፕሮጀክት የራሱ የሆነ ሩፍ ቶፕ ጋርደን እና በስሩ ዘመናዊ የሆነ ሬስቶራንት እና ካፌ የያዘ 600 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ የራሱ የሆነ ባለ ሁለት ወለል የመኪና ማቆምያ ያለው G+12 ህንጻ ነው።

“በጊዜ ግቡ” በሚል መሪ ቃሉ የሚታወቀው ጀንቦሮ ሪል እስቴት በ2012 ዓ.ም ተመስርቶ በ4 ዓመት ጊዜ ውስጥ ቃሉን በመጠበቅ የተመሰገነ እና ለዘመናዊ አኗኗር ምቹ የሆኑ መኖሪያ ቤቶችን ከተሟላ አገልግሎት ጋር አጠናቆ በማስረክብ የታወቀ ሪል እስቴት እንደሆነ ተገልጿል።
ከዚህ በተጨማሪም የተለያዩ ኘሮጀክቶችን በተለያዩ አካባቢዎች በመገንባት ላይ የሚገኘው ጀንቦሮ ሪል እስቴት በመጪው አምስት አመታት ውስጥ 5,000 አፓርትመንቶችን ፣ ቪላዎችን እና የንግድ ሱቆችን ለቤት ገዥዎች ሰርቶ ለማጠናቀቅ በሂደት ላይ ይገኛል፡፡
ጀንቦሮ ሪል እስቴት ባለፉት 4 ዓመታት በገባው ውል መሰረት በአጠቃላይ 210 ቤቶችን ገንብቶ አስረክበዋል።


















