በኢትዮጵያ የሪል እስቴት ዘርፍ ውስጥ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኘው ቴምር ሪል እስቴት በጋርመንት አካባቢ በ1 ሺህ አንድ መቶ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያስገነባውን እና ሁለት የምድር ውስጥ ወለሎችን ጨምሮ ሃያ ፎቆች ያሉት ዘመናዊ ህንፃ ዛሬ ጥቅምት 14 ቀን 2019 ዓ.ም የመጀመሪያ ዙር የቁልፍ ማስረከብ ስነ-ስርዓት አከናውኗል።
በዚህ የርክክብ መርሃ ግብር ላይ 56 የሚሆኑ የንግድ ሱቆች ቁልፍ ለባለቤቶቹ በይፋ የተሰጠ ሲሆን ቀሪዎቹ መኖሪያ አፓርትመንቶች የሚረከቡበት የጊዜ ሰሌዳም ይፋ ተደርጓል።
ህንፃው በአጠቃላይ 136 የመኖሪያ አፓርትመንቶችን እና 56 የንግድ ሱቆችን በውስጡ የያዘ ሲሆን ለአካባቢው የንግድና የኑሮ ትስስር የበኩሉን አስተዋጽዖ ያበረክታል ተብሎ ይጠበቃል።

በርክክብ ስነ-ስርዓቱ ላይ የኩባንያው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጃፈር መሀመድ ባደረጉት ንግግር “ዛሬ ለቴምር ሪል እስቴት ድርጅት ትልቅ የስራ ስኬት የተመዘገበበት ቀን ነው፤ ይህንን ግዙፍ ፕሮጀክት በተያዘለት ጥራትና ደረጃ አጠናቀን ዛሬ ለባለቤቶቹ ስናስረክብ ከፍተኛ ደስታ ይሰማናል” ብለዋል።
ዋና ስራ አስፈፃሚው አክለውም ይህ ውጤት የደንበኞቻችን እምነት እና የማኔጅመንቱና የሰራተኛው ከፍተኛ ጥረት ውጤት ነው።
ቴምር ሪል እስቴት ሁልጊዜም ጥራትን ዘመናዊነትን እና ታማኝነትን መርሆው አድርጎ እንደሚጓዝ ቃል የምንገባ ሲሆን ወደፊትም የሀገራችንን የቤት ፍላጎት ለማቃለል የሚያደርገውን የከተማ ልማት ግንባታ አጠናክሮ ይቀጥላል” ብለዋል።
በመጨረሻም ለዚህ ስኬት አስተዋጽዖ ላደረጉ አካላት በሙሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ምንጭ:- ድሬቲዩብ

















