ጊፍት ሪል እስቴት ሁለተኛውን የአዲስ ዓመት የአፓርትመንትና የንግድ ሱቆች የሽያጭ ኤክስፖ በይፋ አስጀምሯል፡፡
በኤክስፖው እስከ 25% ቅናሽ በማድረግ በ2% ቅድመ ክፍያ ብቻ የቤት ባለቤት መሆን የሚያስችል ዕድል አመቻችቷል፡፡
የሽያጭ ኤክስፖው ከመስከረም 29 እስከ ጥቅምት 8/ 2018 ዓ.ም. የሚካሄድ ሲሆን 1 ሺህ 500 ቤቶች ለሽያጭ ቀርበዋል፡፡
አንጋፋው ጊፍት ሪል እስቴት፣ ሦስት መንደሮችን ጨርሶ ለህብረተሰቡ ባስረከበበት ማግስት፣ አራተኛውን የጊፍት ሜትሮፖሊታን መንደር፣ “የዋና ከተማችን ዋና ከተማ” በሆነው በለገሃር ላይ 4 ሺህ ቤቶችን በጥራት በመገንባት ላይ ይገኛል፡፡
ከነዚህ መካከል የ12 ሺህ ቤቶች ማስፋፊያ አካል የሆኑ በሁለተኛና ሶስተኛ ዙሮች የሚገነቡ 8 ሺህ የመኖሪያ እና የንግድ ቤቶች፣ እንዲሁም በ6 ኪሎ፣ በቦሌ መድሃኒዓለም፣ በፊጋ፣ በ22 ማዞሪያ፣ በተክለሃይማኖት፣ በሲኤምሲ እና በሌሎች አካባቢዎች 4 ሺህ፤ በአጠቃላይ ከ16 ሺህ በላይ ቤቶች ተዋውቀዋል፡፡
ለኑሮ ምቹ በሆኑት መንደሮቻችን፣ ትምህርት ቤ/ቶች፣ የህክምና ተቋማት፣ ሞሎች፣ የመዝናኛ ስፍራዎች ከበቂ የመኪና ማቆሚያ ጋር ተካተዋል፡፡
ጊፍት ሪል እስቴት፣ እስካሁን፣ በ165 ሺህ ካሬሜትር ላይ በሲኤምሲ እና ፈረስ ቤት ሦስት ትላልቅ መንደሮችን ገንብቶ ለማኅበረሰቡ በማስረከብ ተዓማኒነትን አትርፏል፡፡
ምንጭ፡ የኔታ ቲዩብ


















