ሂል ቦተም ፕሮፐርቲስ በአያት አደባባይ ፊት ለፊት የሚገኘውን በዘመናዊ መልኩ የተገነባ ባለ 12 ፎቅ መኖሪያ ቤቶች ዛሬ መስከረም 11 ቀን 2017 ዓ.ም አስመርቋል።
የመኖሪያ አፓርትመንቱ በቅጥር ግቢው ውስጥ ጅም፣ ስፓ፣ የመዋኛ ገንዳ፣ የቴኒስ ሜዳ፣ በቂ የመኪና ማቆሚያ ዘመናዊ አሳንሰር ከመጠባበቂያ ጀኔሬተር ጋር ያሟላ እንደሆነ ተነግሯል።

በዚሁ በተጠናቀቀው አፓርትመንት ግቢ ውስጥ ሁለተኛውን ብሎክ አፓርትመንት በመገንባት እና በመሸጥ ላይ ሲገኝ በተጨማሪም በአይነቱ ለየት ያለ እጅግ ዘመናዊ አፓርትመንት በመሀል ካዛንችስ አዲስ ግንባታ ለመጀመር ዝግጅት አጠናቋል።
ሂል ቦተም በመዝናኛ ማዕከልነቱ ለ16 ዓመታት ህብረተሰቡን በማገልገል የሚታወቀው ሲሆን የህበረተሰቡን ፍላጎት መሰረት በማድረግ በሪል እስቴት ዘርፍ በሰፊው በመሰማራት ራዕዩን አንግቦ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ተነግሯል።
ምንጭ፦ ድሬቲዩብ


















