ሜሪት ፕሮፐርቲስ በተክለሃይማኖት እየገነባ ያለውን ዘመናዊ የንግድ ማዕከል የግንባታ ሂደት በአካል ለማሳየት ያዘጋጀው ልዩ ሜሪት ኤክስፖ መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ.ም. በደማቅ ሁኔታ ተከፈተ።
በመክፈቻው ላይ ከፍተኛ የመንግሥት ሃላፊዎች፣ የሚዲያ ባለሙያዎች እና የተጋበዙ እንግዶች ተገኝተዋል። ኤክስፖውም እስከ መስከረም 29 ቀን 2019 ዓ.ም. ይቀጥላል።
ከ6,700 ካሬ ሜትር በላይ በሆነ ስፋት ላይ የሚገነባው ባለ 5 ፎቅ የንግድ ማዕከሉ በመርካቶ ተክለሃይማኖት አካባቢ ለነጋዴዎችና ለባለሀብቶች ዘመናዊ፣ ምቹና ተግባራዊ የንግድ ቦታ ለመፍጠር እየተገነባ ይገኛል።
የሕንፃው ግንባታም በተያዘለት እቅድ መሠረት እየገሰገሰ ሲሆን በዚሁ ዓመት ለማጠናቀቅ ታቅዷል።


በኤክስፖው የሚገኙ ጎብኚዎች የግንባታውን ሂደት በአካል በመመልከት ስለ ሕንፃው ዲዛይንና የንግድ ቦታዎች መረጃ በማግኘት እንዲሁም ከኩባንያው ባለሙያዎች ጋር በቀጥታ በመወያየት ዕድል ያገኛሉ።
የኤክስፖው ዋና መልዕክትም “አዲስ ነገር ሲገነባ ተጠናቅቆ እስኪታይ መጠበቅ አያስፈልግም” የሚለውን እሳቤ በማጉላት ሜሪት ፕሮፐርቲስ የሚገነባውን በሂደቱ ለማሳየት ያለውን ግልጽነትና እምነት ያሳያል።
ኤክስፖው ሜሪት ፕሮፐርቲስ የጀመረውን የአንድ ዓመት ጉዞ በመገምገም ወደ ቀጣዩ ምዕራፍ የሚያደርገውን ጉዞ የሚያሳይ ሲሆን፣ የኩባንያውን “የታመነ ንብረት” የሚለውን መርህ በተግባር ለማሳየትም ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
ምንጭ፦ ጣፋጭ ሕይወት


















