በሱፍቃድ ሪል እስቴት ለፋና ላምሮት 5ኛው ዙር አሸናፊ የ300,000 ሽልማት ለማበርከት ቃል ገባ
የበሱፍቃድ ሪል እስቴት ልማት ድርጅት ከምንጃር ሸንኮራ፣ አረርቲ ከተማ 300,000 ብር የማበረታቻ ሽልማት አብስሯል።
ሪል እስቴት ልማት ድርጅቱ ልዩ ልዩ የበጎ አድራጎት ሥራዎችን በመሥራት አርዓያ ሲሆን፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ወጣቶች ችሎታቸውን እንዲያሳድጉና ሕልማቸውን እንዲኖሩ እየደገፈ ይገኛል።
አሁንም የፋና ላምሮት 5ኛው ዙር የአሸናፊዎች አሸናፊ ላይ በብርቱ ችሎታዋ በከፍተኛ ብቃቷ አሸናፊ ለሆነችው ከዚህ ቀደም ወደ አሸናፊዎች አሸናፊ ዙር በብቃት ባለፈችበት ወቅት 50,000 ሺህ ብር ማትጊያ ያበረከተው ድርጅቱ በድጋሜ ወጣት እየሩሳሌም አሰፋን ለማበረታታት የ300,000 ብር ሽልማት ለማበርከት ቃል ገብቷል።
በፋና ላምሮት 5ኛው የአሸናፊዎች አሸናፊ እየሩሳሌም አሰፋ 4ኛ በመሆን ያጠናቀቀች ሲሆን ከፋና ላምሮት የ300 ሺህ ብር ተሸላሚ ሆናለች።
ምንጭ፡ Besufkad Realstate


















