ኦቪድ ሪል እስቴት በጅማ ከተማ በሚያከናውነው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት የመጀመሪያውን ዙር የቤቶች ሽያጭ ዛሬ ማለዳ በይፋ አስጀምሯል።
ኩባንያው በዚህ ፕሮጀክት ግንባታቸው 80 በመቶ በደረሱና በ6 ወራት ጊዜ ውስጥ ሙሉ ለሙሉ ተጠናቅቀው በሚረከቡ 3 ብሎኮች የመኖሪያ ቤቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ መሸጥ መጀመሩን ያበሰረ ሲሆን፣ ለደንበኞች የሚያመቹ የተለያዩ የክፍያ አማራጮችን ማዘጋጀቱንም ገልጿል።

በርካቶችን የቤት ባለቤት በማድረግና የጅማ ከተማን ገጽታ በመቀየር ረገድ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት የተነገረለትና ቦዬ ተብሎ በሚጠራው የከተማዋ አካባቢ የሚገኘው ይህ ፕሮጀክት በአጠቃላይ 48 ብሎኮችን የሚያካትት ሲሆን፣ የግንባታ ስራውን በጥራትና በፍጥነት የሚያከናውነው እህት ኩባንያው ኦቪድ ኮንስትራክሽን ነው።
ምንጭ፡ ኦቪድ ሆልዲንግ ኮሙዩኒኬሽንና የሕዝብ ግንኙነት


















