ባማኮን ሪል እስቴት በ6 ቢሊየን ወጪ በመሐል ካዛንችስ ላይ አስገንብቶ ለአገልግሎት ዝግጁ ያደረገውን የመኖሪያ እና የንግድ አፓርትመንት ዛሬ መስከረም 8/2018 ዓ.ም በይፋ አስጀምሯል።
ጋላክሲ ፊኒሽንግ ሞል 2000 ካሬ ላይ ያረፈ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ባለ 24 ወለል እጅግ ዘመናዊ የመኖሪያ እና የንግድ አፓርትመንት ሲሆን የኪነ ሕንጻ ባለሙዎችን፣ ሻጭ እና ገዥዎችን፣ አቅራቢዎችን፣ ዲዛይነሮችን እና ሌሎችንም በአንድ ጣሪያ ስር ያሰባሰበ የመኖሪያ እና የንግድ አፓርትመንት እንደሆነ የባማኮን ሪል እስቴት መስራችና ስራ አስኪያጅ የሆኑት ኢ/ር ግርማ ገላው ገልጸዋል።

ኢ/ር ግርማ አክለውም ጋላክሲ ፊኒሺንግ ሞል የኤሌክትሪካል ሥራዎችን፣ የመታጠቢያ እና የንጽህና መጠበቂያ ክፍሎች መሥሪያ ቁሶችን፣ የወለል እና የግድግዳ ሥራዎች ማጠናቀቂያ ማቴሪያሎችን፣ ዘመናዊ የፊኒሽንግ ማቴሪያሎችን፣ በአጠቃላይ ሁሉንም የፊኒሽንግ ማቴሪያሎችን በአንድ ጣሪያ ስር አቀናጅቶ የያዘ ዘመናዊ ሞል ነው፡
፡
ጋላክሲ ፊኒሺንግ ሞል እስከ 4ኛ ፎቅ ድረስ 173 ሱቆችን የያዘ ሲሆን የግንባታ መሠረት ከማስቀመጥ እስከ ፊኒሺንግ ሥራ ድረስ በራሱ ድርጅቶች ሙሉ አቅም የተሠራ፣ የራሱ ምቹ እና በቂ የተሽከርካሪ ማቆሚያ ያለው እንዲሁም በአካባቢው ላይ በከተማ አሥተዳደሩ እየተገነቡ ያሉ የተሽከርካሪ ማቆሚያዎች፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎች፣ የመዝናኛ ስፍራዎች፣ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቻርጅ ማድረጊያዎች እና ሌሎችም አስፈላጊ ነገሮች የተሟሉለት ነው፡፡
በሪልእስቴት ዘርፉ አዳዲስ የፈጠራ እና የልህቀት መመዘኛዎችን በመተግበር በምሥራቅ አፍሪካ በዘርፉ መሪ የመሆን ርዕይ ያነገበው ባማኮን ሪል እስቴት አሁን ላይ በአዲስ አበባ ካዛንችስ፣ ባምቢስ፣ አትላስ፣ ፍሬንድሺፕ ፓርክ፣ቦሌ ኤርፖርት ቪው ፣ሜክሲኮ እና ቡልቡላ ‹‹ሳይቶች›› የመኖሪያ እና የንግድ ቤቶችን በከፍተኛ ጥራት እና ፍጥነት እየሠራ የሚገኝ ግዙፍ ሪል እስቴት ነው፡፡
ምንጭ፡ ድሬትዩብ


















