ቫሞስ ሪል እስቴት አርቲስት ነጻነት ወርቅነህን የብራንድ አምባሳደር አድርጎ የሾመ ሲሆን የቫሞስ ሪል እስቴት የመኖሪያ ቤቶችን ለአንድ አመት ያህል ያሰትዋውቃል። በእለቱ በስካይላይት ሆቴል በቫሞስ ሪል እስቴት እና በአርቲስት ነጻነት ወርቅነህ መካከል የፊርማ ስነ ሥራአት የተከናወነ ሲሆን አርቲስት ነጻነት ወርቅነህ ለአንድ አመት 3.7 ሚሊዮን ብር እንደተከፈልውም ታውቋል።

አርቲስቱ ከፊርማ ስነ ሥራዓቱ በኋላ እንደተናገረው ከዚህ በኋላ በቴሊቪዝን፣ በሬድዮ እንዲሁም በፖስተር ከቫሞስ ጋር ታዩኛላችሁ ብሏል።
የቫሞስ ሪል እስቴት ሥራ አስኪያጅ አቶ ግርማ ዋቅሹም በፊርማ ሥነ ሥራዓቱ ላይ ባደርጉት ንግግር “አርቲስት ነጻነት ቫሞስ የሚገነባቸውን የመኖሪያ አፓርትመንቶች ለማሰትዋወቅ ፈቃደኛ በመሆኑ በጣም ደስተኞች ነን። እሱ ሸክማችንን ያቃልልናል ብለን እናምናለን።” ብለዋል።

በ2009 ዓም ከ83 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ካፒታል የተመሰረተው ቫሞስ ትሬዲንግ ኃ/ይተ/የግ/ማ በሆቴልና ቱሪዝም፣ በኮንስትራክሽን፣ በሪል እስቴት ማልማት እና ተጓዳኝ የንግድ ስራዎች የተሰማራ ድርጅት ነው።

ቫሞስ ሪል እስቴት በለቡ አካባቢ በ 2717 ካሬ ሜትር ላይ ባለ ሁለት መኝታ የመኖሪያ እና የንግድ ቤት አፓርትመት መገንባቱ ይታወቃል። በቀጣይም በካዛንቺስ እና ቦሌ ፍሬንድሺፕ ሆቴል አካባቢ አለምአቀፍ ደረጃዎችን ያሟሉ የመኖሪያ አፓርትመንቶችን ገንብቶ ለገበያ የሚያቀርብ መሆኑም ተገልፀዋል።

















