አርቲስት አብርሐም ወልዴ በኢትዮጵያ ውስጥ ከተከፈሉ ክፍያዎች ሁሉ ትልቁ ክፍያ ተከፍሎት አምባሳደር ሆነ።
ከ30 አመት በፊት ወደ ቤት ግንባታ ገብቶ በርካታ የመኖሪያ ቤቶችን በመሥራት ለቤት ፈላጊዎች ያሥረከበው ጊፍት ሪል እስቴት ሰኔ 19/2016 ዓ/ም ተወዳጁን አርቲስት አብርሐም ወልዴን ለሶስት አመት በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ አርቲስቶች ከተከፈላቸው በላይ ትልቁን ክፍያ ከፍሎ የድርጅቱ የብራንድ አምባሳደር አድርጎ ሾመ።
በፕሮግራሙ ላይ ከፍተኛ አመራሮች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። አብርሐም ወልዴ ጊፍት ሪል እስቴትን አሁን ካለበት ስሙ ከፍ ለማድረግ እና ለማስቀጠል ኃላፊነትን ተቀብሎ ተፈራርሟል።
አርቲስት አብርሐም ወልዴ በመልዕክቱ ጊፍት የምኮራበትና ምርጫዬ ስለሆነ በደስታ ነው አምባሳደርነቴን የተቀበልኩት ስለመረጣችሁኝ ሁላችሁንም አመሠግናለሁ የተጣለብኝን አደራም በብቃት ለመወጣት ቃል እገባለሁ ሲል መልዕክቱን አስተላልፏል።
ጊፍት እስከ አሁን ባደረገው ጉዞ፣ ከ150 ሺህ ካሬ በላይ በሆነ ቦታ ላይ ሶስት ዘመናዊ መንደሮችን በሲኤም ሲ እና ፈረስ ቤት አካካቢ/በለሚኩራ ክፍለ ከተማ/ገንብቶ አስረክቧል፡፡
የልማት ግስጋሴውን በመቀጠል፣ አሁምን በአዲስ አበባ እምብርት/ማለትም በቦሌ፣ በአትላስ፣ በለገሃር፣ በ22፣ በስድስት ኪሎ፣ በተክለኃይማኖትና በፊጋ አካባቢዎች ዘመኑን የዋጁ ወለላቸው ከ20 በላይ የሆኑ ዘመናዊ መንደሮችን፣ የንግድ እና የመኖሪያ አፓርትማዎች፣ ሞሎችን ግንባታ እና ዲዛይን መጀመሩ ተገልጿል።
አብዛኞቹም በሶስት ዓመት ጊዜ ውስጥ የሚጠናቀቁ በመሆናቸው ሽያጭ መጀመሩን ተናግረዋል።
ምንጭ፦ የኔታ ቲዩብ


















