በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት እና የግል አጋርነት ጽህፈት ቤት የመሬት ዝግጅት እና የወሰን ጉዳዮች አማካሪ ዕጩ ዶ/ር አብዲ ፉፋ ዲዛይኑን ይፋ ያደረጉ ሲሆን መተማመንና አብሮ በጋራ መስራት ለኢኮኖሚያዊ ዕድገት ትልቅ መሰረት ነው በማለት ገልፀው የግል ሴክተሩ ከመንግስት ጋር አብሮ በጋራ ሲሰራ ከፍተኛ የሆነ ስኬት ይኖራል በማለት ገልፀው አፍሪካ ሆልዲንግ ግሩፕን እንደሚያግዙ ተናግረዋል
የሪል እስቴት ግንባታው በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል አካባቢ ተክለሃይማኖት ወይም በተለምዶ ሜዳ ጋራጅ የሚባለው አካባቢ ሲሆን ከተሰጠው 10 ሄክታር መሬት 1 ሄክታሩ ላይ እየተገነባ የሚገኘው ጎዶ ሪል ስቴት ዛሬ በተካሄደው መርሃግብር ላይ በርካታ ባላድርሻ አካላትና የመንግስት ባለስልጣናት በተገኙበት ዲዛይኑ ይፋ የተደረገው
ጥቁር አንበሳ አካባቢ እንደሚገነባ የተነገረለት ይህ ዘመናዊ የመኖሪያ መንደር፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዘመናዊ የተባሉ ቴክኖሎጂዎችን ያካተተ እንደሆነ የድርጀቱ ሥራ አስኪያጅ አቶ ደረጄ ማሙዬ ገልጸዋል
የሪል ስቴቱ አማካሪ ዶ/ር ኢንጂነር ከሊል አርሙር እንደተናገሩት ሪል ስቴቱ ለነዋሪዎች ምቹ በሆነ ቦታ የሚገነባ እና የተለያዩ አዳዲስ ቴክኖሎጂ የሚገጠምለት መሆኑን እንዲሁም ዘመናዊትን ሙሉ በሙሉ ተላብሶ የሚሰራ ነው ብለዋል
በ27 ቢሊዮን ብር ወጪ ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ባካተተ ሁኔታ የሚገነባው ጎዶ ”Godo housing and smart real state” የሚል ስም የተሰጠው የመኖሪያ መንደሩ የብረት ፍጆታን መቀነስ የሚያስችሉ አዳዲስ የሀብት ቁጠባ ቴክኖሎጂዎችን በጥቅም ላይ እንደሚያውል ተጠቁሟል
አቶ ደረጄ አክለውም በተጨማሪም ድርጅቱ ከዚህ በወጪ ንግድ፣ በምግብ ዝግጅትና እንጀራ መጋገር፣ በምርት ሽያጭ፣ በድንጋይ መፍጨት እንዲሁም በትምህርት ዘርፍ ተሰማርቶ እንደሚገኝ ገልፀዋል
በሚቀጥሉት 5 ዓመታት 500 ሺህ ቤቶችን ለመገንባት መታቀዱ የተገለፀ ሲሆን አፍሪካ ሆልዲንግ ግሩፕ (African Holding Group) ለአፍሪካ ትውልዶች ሀብት ለማፍራት እና የኢኮኖሚ ለውጥ ለማምጣት የተቋቋመ የባለአክሲዮኖች ማህበር ድርጅት ነው
ሪል ስቴቱ 26 ሊፍቶች፣ ከ2 ሚሊዮን ሊትር በላይ ውኃ ማጠራቀሚያ፣ የሄሊኮፕተር ማረፊያ፣ የሕክምና አምቡላንስ አገልግሎት እንዲሁም የአደጋ ጊዜ መጠበቂያ እና የሕፃናት መጫወቻ ስፍራዎችን አጠቃሎ የያዘ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን ቅንጡ የመኖሪያ መንደር ስለመሆኑ ተገልጻል።
ምንጭ፦ Arada Fm (ሰናይት በየነ)

















