ኪ ሃውሲንግ ፋይናንስ ሶሉሽን መስፈርቱን አሟልተው ከተመዘገቡ 13 ሺህ 75 ደንበኞቹ መካከል ለ600 ተመዝጋቢዎች ባለ 1፣ ባለ 2 እና ባለ 3 መኝታ የመኖሪያ ቤቶች የዕጣ ማውጣት ሥነ-ሥርዓት አካሄደ።
ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የተካሄደው ይህ የዕጣ ማውጣት መርሃ-ግብር በአራቱም ዙሮች የተመዘገቡ ቤት ፈላጊዎችን ያካተተ ሲሆን፣ በዕጣው የተካተቱት የመኖሪያ ቤት ዓይነቶችና የባለዕድለኞች ቁጥር እንደሚከተለው ተከፋፍሏል፦
- 75 ባለ አንድ መኝታ ቤቶች
- 175 ባለ ሁለት መኝታ ቤቶች
- 250 ባለ ሦስት መኝታ ቤቶች
በዚህም በድምሩ ለ500 እድለኞች የቤት ዕጣ የወጣ ሲሆን፣ በተጨማሪም ለአንደኛ ዙር ተመዝጋቢዎች በተደረገ የዕጣ ማውጣት ለ100 ተመዝጋቢዎች እድሉ ደርሷቸዋል። በአጠቃላይ በዕለቱ 600 የቤት ፈላጊዎች የመኖሪያ ቤት ባለቤት መሆን ችለዋል።
ኪ ሃውሲንግ እስካሁን ባከናወናቸው አራት የምዝገባ ዙሮች ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ደንበኞች አስተናግዷል። በዚሁ መሠረት፦
- በ1ኛ ዙር፦ 9,253 ተመዝጋቢዎች
- በ2ኛ ዙር፦ 2,629 ተመዝጋቢዎች
- በ3ኛ ዙር፦ 1,503 ተመዝጋቢዎች
- በ4ኛ ዙር፦ 3,172 ተመዝጋቢዎች መመዝገባቸው ተገልጿል።
ምንጭ:- አሐዱ ሬዲዮ
















