ካቮድ ኮሜርሻል ካዛንቺስ ላይ ዘመናዊ የንግድ ሞል ለመገንባት በዝግጅት ላይ እንዳለ በዛሬው እለት በሰጠው መግለጫ አስታውቋል
ካቮድ ይህን የንግድ ማዕከል የሚሰራው ከፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ጋር እንደሆነ የገለፀ ሲሆን ከቦታው ላይ የተነሱ ነጋዴዎችን በማደራጀት ቅናሽ ተደርጎ እንደተሰጣቸው ተገልጿል።
የንግድ ማዕከኩ በውስጡ ከበቂ በላይ የመኪና ማቆሚያ ቦታ ፣ ዋተር ፖርክ ፣ሲኒማ እና የመዝናኛ ስፍራዎች ፣የሴቶች እና የወንዶች ውበት መጠበቂያዎች ፣ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ ሱቆች ፣ካፌ ፣ ሬስቶራንት እና ላውንጅ እንዲሁም ፈጣን ፖኖራሚክ ሊፍት እና እስከሌተርን ያካተተ እንደሆነ የድርጅቱ የሽያጭ ባለሙያ አቶ ጀማል አብዱልቃድር ገልጸዋል።
አቶ ጀማል አክለውም የንግድ ማዕከሉ ግንባታ በ6- 9 ወር የሚጠናቀቅ ሲሆን ይህ የግንባታ ፕሮጀክት ካቮድ ለመገንባት ካቀዳቸው 17 ፕሮጀክቶች ውስጥ 4ኛው ነው ብለዋል።
ሳይቱ የሚገኘው ካዛንቺስ የድሮ 6ኛ ፖሊስ ጣቢያ ጋር ሲሆን 6,762 ካሬ ላይ ያረፈ 2B + G + 11 እንደሆነ ተነግሯል
በአሁን ሰአት ካቮድ ካዛንቺስን ጨምሮ በመገናኛ በ6 ኪሎ አፍንጮ በርና በሽሮሜዳ ላይም ሌላ ዘመናዊ ሞል እየገነባ እንደሚገኝ ተገልጿል።
ምንጭ፡ ድሬትዩብ


















