የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ በከተማው በተለያዩ አካባቢዎች በጋራ መኖሪያ ህንፃ ላይ እና የኮሪደር ልማት በተሰራባቸው አካባቢዎች የሚገኙ 336 የመንግስት ንግድ ቤቶችን ባሉበት ሁኔታ ለኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በጨረታ አወዳድሮ በኪራይ ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡
ቢሮው ለኪራይ ያቀረባቸውን የንግድ ቤቶች በጨረታ ተወዳድሮ መከራየት የሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት በቢሮ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከሐምሌ 18/2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ነሐሴ 2/2017 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ድረስ ባሉት 15(አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት (ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ) በኦንላይን (https://ad dishousebid.gov.ct) ሲስተም ወይም በአካል ዘወትር በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ምሽት 1፡00 ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 1,000.00 /አንድ ሺህ ብር በመክፈል፣ ከዚህ በታች ከተዘረዘሩት ቦታዎች የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላል፡፡

ምንጭ፡ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ


















