የአንደኛ ዙር የንግድ ቤት ኪራይ ጨረታ ውጤት ይፋ ስለማድረግ፤
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ በከተማው በተለያዩ አካባቢዎች በጋራ መኖሪያ ህንፃ ላይ እና የኮሪደር ልማት በተሰራባቸው አካባቢዎች የሚገኙ የመንግስት ንግድ ቤቶችን በጨረታ አወዳድሮ በኪራይ ለማስተላለፍ ከሐምሌ 18 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ግልፅ ጨረታ ፍላጎት ላላቸው ተወዳዳሪዎች ክፍት በማድረግ ከነሐሴ 12/2017 እስከ ነሐሴ 15/2017 ድረስ ተጫራቾች በተገኙበት ጨረታው የተከፈተ መሆኑ ይታወቃል፡፡
በዚህም መሰረት የጨረታው ውጤት ተጠናቅሮ የተጠቃለለ በመሆኑ የአንደኛ ዙር የመንግስት ንግድ ቤቶች ጨረታ ውጤት በዚህ ማስታወቂያ ይፋ የተደረገ መሆኑን እየገለፅን ተወዳዳሪዎች ከዚህ በታች በተያያዘው ሰንጠረዥ ውጤቱን እንድታዩ እናሳውቃለን፡፡
በውጤቱ ላይ ቅሬታ ያላችሁ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ይፋ ከተደረገበት ነሐሴ 30 ቀን 2017 ጀምሮ ባሉት 07 ተከታታይ የሥራ ቀናት(ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ) ቅሬታችሁን በአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ 12ኛ ፎቅ ለቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ምንጭ፡ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ


















