በኦሮሚያ ክልል አዳማ ከተማ የመኖርያ ቤት ፍላጎት ላይ የሚታየውን ችግር መፍታት ያስችላል የተባለለት የጋራ መኖሪያ ቤትና የውስጥ ለውስጥ አስፓልት መንገድ ፕሮጀክቶች ተመረቁ።
በምርቃት መርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የአዳማ ከተማ ከንቲባ ኃይሉ ጀልዴ መንግስት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ጂ+5፤ 27 ብሎክ የጋራ መኖርያ ቤቶች በዘመናዊ መልኩ በአራት ወራት ውስጥ ተገንብተው ተጠናቀዋል ብለዋል።
አንዶዴ የጋራ መኖሪያ ቤት በልማት ስራዎችና በኢንቨስትመንት ምክንያት የተነሱ የልማት ተነሺዎች የሚሰጥ መሆኑም ተገልጿል።
በሥነ ሥርዓቱ ላይ ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎችን ጨምሮ የኃይማኖት አባቶች አባ ገዳዎች ሀደ ሲንቄዎች የሀገር ሽማግሌዎች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
ምንጭ፡ ሀገሬ ቴቪ


















