የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን አገራዊ ለውጡን መነሻ በማድረግ ባካሄደው ሁለንተናዊ ተቋማዊ ሪፎርም ገቢውን ከ41 እጥፍ በላይ ማሳደግ መቻሉን አስታወቀ።
ኮርፖሬሽኑ ባወጣው ይፋዊ መረጃ መሠረት፣ በ2018 በጀት ዓመት ከፍተኛ የገቢ እድገትና ታሪካዊ የተባለ ስኬት ሊመዘገብ የቻለው በተካሄደው ጥልቅ የተቋም ማሻሻያ እና በመላው የድርጅቱ ሰራተኞች በኩል በተደረገው የላቀ አስተዋጽኦ ነው ተብሏል።
ይህንን ታሪካዊ ስኬት አስመልከቶ ኮርፖሬሽኑ ለመላው ተቋማዊ ሰራተኞቹ የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት ያስተላለፈ ሲሆን፣ ላበረከቱት የላቀ አስተዋጽኦ እና ላሳዩት ቁርጠኝነት ላቅ ያለ ምስጋናውን አቅርቧል።
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን “በአዲስ ምዕራፍ ለተሻለ ነገ!” በሚል መሪ ቃል አዳዲስ የቤቶች ግንባታ፣ ነባር ንብረቶችን ማደስ እና የንብረት እሴት የማሳደግ ሥራዎችን በስፋት ሲያከናውን መቆየቱ ይታወቃል።
ምንጭ:- የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን
















