በዴሉክስ ፕሮፐርቲስ እየተገነቡ ያሉ የሪል እስቴት አፓርትመንት መኖሪያ ቤቶችን ለሚገዙና የባንኩን የብድር አሰጣጥ መመሪያ የሚያሟሉ ከሀገር ውጪ ለሚኖሩ የዲያስፖራው ማህበረሰብ በወጋገን ባንክ በኩል የፋይናንስ ብድር ድጋፍን እንደሚያደርጉ ተነግሯል።
በሁለቱ ድርጅቶች መካከል የተደረገዉ ስምምነት የሪል እስቴት ቤት ገዥዎች የፋይናንስ ብድር አቅርቦት ስምምነት ዝቀተኛ ወለድ እንዳለው የተገለጸ ሲሆን እንዲሁም ለ25 ዓመታት ተከፍሎ የሚጠናቀቅ እና የአፓርትመንት ቤቱን ዋጋ እስከ 80% በብድር የሚሸፈን መሆኑ በመድረኩ ተገልጿል።
ስምምነቱ በዋነኝነት በሀገራችን እያደገ የመጣውን የመኖሪያ ቤት ፍላጎት እና የተረጋገጠ የመኖሪያ ቤት አቅርቦት እጥረትን ለማጣጣም ተግዳሮት ከሆኑት ምክያቶች አንዱ እና ዋነኛ የሆነውን የፋይናንስ ችግርን ለመቅረፍ የተደረገ ስምምነት መሆኑ ተገልጿል።
ከወጋገን ባንክ ጋር የተደረገው ስምምነት ዴሉክስ ፕሮፐርቲስ ዘመናዊ አፖርትመንት ቤቶችን ገንብተው ለተጠቃሚዎች ያለምንም የፋይናንስ ችግር የቤት ባለቤት የሚሆኑበትን ዕድል ስምምነቱ መፍጠሩን ተነግሯል ።
ምንጭ፡ Arts Tv















