የ2016 ዓ.ም ባላገሩ ምርጥ የፍፃሜ ውድድት የክብር ስፓንሰር በመሆን አንደኛ ለሚወጣው ተውዳዳሪ የ3 ሚሊዮን ብር ስጦታ አበርክቷል።
በዚህም መሰረት የውድድሩ ቀን የጊፍት ሪል እስቴት ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ገብረየሱስ እጋታ ከተሰጥዖ ጎን ቆመው ትውልድን ለመቅረፅ ላደረጉት አስተዋፅዖ የማስታወሻ ስጦታ ከባላገሩ ምርጥ ተበርክቶላቸዋል። አቶ ገብረየሱስ ኢጋታ በበኩላቸው ለፍፃሜ ለደርሱት የጥበብ ሙያተኞች እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።
በኢትዮጵያ ውስጥ ፈር ቀዳጅ ከሆኑ የሪል እስቴት ኩባንያዎች አንዱ የሆነው ጊፍት ሪል እስቴት በሲኤምሲ አካባቢ አንድ መለስተኛ መንደር ገንብቶ በማስረከብ ስራውን የጀመረ ሲሆን በመቀጠልም ከፀሐይ ሪል እስቴት ጀርባ በ90,000 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ የሪል እስቴት መንደር ገንብቶ አስርክቧል።

ሀያት አካባቢ በ56,000 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ሞልን ያካተተ መንደር ግንባታውን በማጠናቀቅ ላይ ይገኛል።
እንዲሁም ቦሌ አካባቢ ባለ 26 ፎቅ፣ በቦሌ ዋና መንገድ ላይ ባለ 22 ፎቅ፣ በግንባታ ላይ ያሉ ሳይቶች ናቸው።
ተክለሀይማኖት፣ ስድስት ኪሎ አሜሪካ ኤምባሲ አካባቢ፣ ፊጋ እና የመሰሰሉት አካባቢ ግንባታ ለመጀመር በዝግጅት ላይ ይገኛል።
ከአዲስ አበባ መስተዳደር ጋር በመሆን 12,000 ቤቶችን ለመገንባት ተፈራርሞ፣ ቦታ ተረክቦ ግንባታ ለመጀመር በመንቀሳቀስ ላይ እንደሚገኝም የዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ገብረየሱስ ገልፀዋል።


















