አመታዊው የሪል እስቴት እና የቤት ኤክስፖ ለሰባተኛ ጊዜ ለማዘጋጀት የሚያስፈልጉትን ቅድመ ዝግጅቶችን በማጠናቀቅ ከታህሳስ 18, 19 እና 20 ቀን 2017 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ኢንተርናሽናል ሆቴል እንደሚካሄድ አዘጋጁ 251 ኮሙኒኬሽን ኤንድ ማርኬቲንግ ገልጿል።
ኢትዮጵያ ከጊዜ ወደ ጊዜ አዳጊ ኢኮኖሚ እያስመዘገበች ያለችበት ወቅት መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን፣ በዚሁ ረገድ በቤት ልማት ዘርፍ አያሳደገች ያለችውን እድገት ተከትሎ የግሉ ዘርፍ የሚኖረውን ሚና ለማሳደግ እንዲረዳ ታስቦ መዘጋጀት የጀመረው ኢቲ ሪል ስተት እና ሆም ኤክስፖ የሪል እስቴት አልሚዎችን ከቤት ባለቤቶች፣ ከገዥዎች፣ ከሻጮች እና ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር የሚያገናኝ ቀዳሚ ኤግዚቢሽን እንደሆነ ተነግሯል።
በኤክስፖ በኢትዮጵያ የሪል እስቴት እና የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪዎች ከፍተኛ ባለድርሻ አካላት ከፍተኛ አልሚዎችን፣ ባለሀብቶችን፣ የፋይናንስ ተቋማትን፣ የቤት ገንቢዎችን እና የቤተ ውበት ባለሙያዎችን ጨምሮ በአንድ ላይ ያሰባስባል ተብሏል።
የ251 ኮሙኒኬሽን መስራች አቶ አዲስ አለማየሁ “የዘንድሮው ኤክስፖ በኢትዮጵያ ሪል እስቴት ዘርፍ ትልቅ ፋይዳ ያለው ክስተት ሲሆን በኢንዱስትሪው ውስጥ ከፍተኛ ተደማጭነት ያላቸውን ተዋናዮችን ያሰባስባል። ዘላቂ ልማትን፣ ፈጠራን እና ኢንቨስትመንትን የሚያበረታታ መስተጋብራዊ መድረክ በመፍጠር የዘርፉን እድገት ለመደገፍ ቁርጠኛ ነን ብሏል።
በ7ኛው አመታዊ ሪል እስቴት እና የቤት ኤክስፖ ከኤግዚብሽኑ በተጨማሪ በኢንዱስትሪው ላይ ከሚገኙ ዋና ባለድርሻ አካላት እና ከመንግስት ተወካዮች ጋር የመገናኘት እድል እንደሚፈጥር ተነግሯል በተጨማሪም የፓናል ውይይትም ይኖራል።
ምንጭ፦ FastMereja

















