ተዋናይት ናርዶስ አዳነ ዳጎስ ባለ ገንዘብ ከላይፍ ታይም ፕሮፐርቲስ ጋር የብራንድ አምባሳደርነት የስራ ውል ስምምነት በዛሬው እለት ተፈራርማለች፡፡
በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ እንደተገለጸው የአርቲስቷ የአምባሳደርነት ስምምነት የሚቆየው ለሁለት አመት ነው፡፡
እንዲሁም ተዋናይት ናርዶስ አዳነ በላይፍ ታይም ፕሮፐርቲስ ለቴሌቪዥን፤ ቢል ቦርድ እና ሶሻል ሚዲያዎች ላይ ማስታወቂያዎች ለመስራት ተፈራርማለች፡፡

ላይፍ ታይም ከተዋናይት ናርዶስ አዳነ ጋር ህዝቡ ጋር የነበረውን ተደራሽነት በተሻለ መልኩ ለማጎልበትና የተለያዩ ስራዎችን በጋራ ለመስራት ስምምነቱን እንዳረገ ተነግሯል፡፡
ላይፍ ታይም ፕሮፐርቲስ በአለም አቀፍ የሪል እስቴት ስራዎች ላይ የተሰማራ ድርጅት ሲሆን በ4 ኪሎ አካባቢ አፓርታማ ሰርቶ ያስረከበ መሆኑን መግለጹ ይታወሳል፡፡
እንዲሁም በአሁኑ ወቅት በቦሌ መድሀኒአለም አካባቢ ባለ21 ፎቅ አፓርታማ እያስገነባ እንደሆነ ተናግሯል፡፡
ምንጭ፡ ድሬ ትዩብ


















