ኦቪድ ሪል እስቴት በአራት ኪሎ ሳይት ለተረከቡ ደንበኞቹ የአዲስ ዓመት ስጦታ አበረከተ፤ ለኢትዮጵያ ሴት አርቲስቶች ማህበር የ100 ሺህ ብር ድጋፍ አደረገ።
ኦቪድ ሪል እስቴት የ2019 አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በአራት ኪሎ ጥይት ቤት ሳይት ቤቶቻቸውን ሙሉ በሙሉ ተረክበው መኖሪያ ላደረጉ ደንበኞቹ በቤታቸው በመገኘት ድንገተኛ (Surprise) የበዓል ስጦታዎችን አበረከተ።
በዚሁ መርሃ ግብር ላይ የኦቪድ ሪል እስቴት የማርኬቲንግ ዲፓርትመንት ኃላፊ አብይ ንጉሴ፣ የሽያጭ ዲፓርትመንት ኃላፊ ኤርሚያስ ሙሴ፣ የኢትዮጵያ ሴት አርቲስቶች ማህበር ፕሬዝዳንት አርቲስት ልዩ ገዙ እና የሚዲያ ተቋማት ተወካዮች በመገኘት የኦቪድ ሪል እስቴት ሳይቶችን እና ደንበኞችን ጎብኝተዋል።
በጉብኝቱም በአራት ኪሎ ጥይት ቤት ሳይት ከታቀዱት 8 መደበኛ ብሎኮች ውስጥ 3ቱ ተጠናቀው ለደንበኞች የተረከቡ ሲሆን፣ ቀሪዎቹ 5 ብሎኮች አዲሱን የኩም ካንግ አልሙኒየም ፎርም ወርክ (Kumkang Aluminum Formwork) ቴክኖሎጂ በመጠቀምና በ24/7 የሥራ ባህል ተገንብተው በ2019 ዓ.ም ሙሉ በሙሉ ለአገልግሎት እንደሚበቁ ተብራርቷል።
የጉብኝት ቡድኑ በተጨማሪም በቦሌ መድኃኔዓለም እና በቦሌ ቡልቡላ O.G.G.C ሳይቶች በመገኘት የፕሮጀክቶቹን የግንባታ ሂደትና በቀጣይ የሚከናወኑ እቅዶችን ተመልክቷል። የመርሃ ግብሩ ማጠቃለያ በኦቪድ ሪል እስቴት ዋና መስሪያ ቤት በምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሰናይ ሸዋፈራው የመዝጊያ ንግግር የተከናወነ ሲሆን፣ ድርጅቱ ለኢትዮጵያ ሴት አርቲስቶች ማህበር የ100,000 ብር የአዲስ ዓመት ስጦታ አበርክቷል።
ኦቪድ ሪል እስቴት በአሁኑ ወቅት በአራት ኪሎ ጥይት ቤት፣ በጉለሌ፣ በቦሌ ቡልቡላ O.G.G.C፣ በጫካ፣ በቦሌ መድኃኔዓለም እና በቦሌ ጃፓን በሚገኙ ሳይቶቹ የመኖሪያ ቤቶችና የንግድ ሱቆች ሽያጭ በማካሄድ ላይ ይገኛል።
















