የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በጋራ ህንጻዎች ስር የሚገኙ ንግድ ቤቶችን በግልጽ ጨረታ ሊሸጥ መሆኑን አስታወቀ
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በአዋጅ ቁጥር 84/2016 በአንቀጽ 22 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በጋራ ህንጻዎች ስር የሚገኙ ንግድ ቤቶችን በ3ኛ ዙር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በሽያጭ ማስተላለፍ እንደሚፈልግ አስታወቀ።
በዚሁ መሰረት በካፒታል ፕሮጀክት ተገንብተው በተለያዩ ሳይቶች የሚገኙ ንግድ ቤቶችን ለግልጽ ጨረታ ያቀረበ ሲሆን፣ ተወዳድሮ መግዛት የሚፈልግ ማንኛውም አካል በሂደቱ መሳተፍ እንደሚችል ተገልጿል።

ይህንኑ የጨረታ ሂደት በመከተል ንግድ ቤቶቹን መግዛት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከጥቅምት 25 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሕዳር 18 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ ባሉት 21 የሥራ ቀናት ውስጥ ማግኘት እንደሚችል ተመላክቷል።
በዚህ የሽያጭ ሂደት ውስጥ ቅዳሜን ሙሉ ቀን ጨምሮ ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ ምሽት 11፡30 ሰዓት ድረስ በአካል በመቅረብ መስተናገድ የሚቻል መሆኑ ተገልጿል።
ተጫራቾች የማይመለስ 1,000 (አንድ ሺህ) ብር በመክፈል ከተገለጹት ቦታዎች የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚቻል መሆኑን አሳውቋል።
ምንጭ:- የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት


















