በሽያጭ ሥልጠና፣ በሪል እስቴት አማካሪነት እና በጠንካራ የሽያጭ ቡድን ግንባታ ከ22 ዓመታት በላይ የካበተ ልምድ ያላቸው አቶ ቢንያም ያዕቆብ በአኮያ ፕሮፐርቲስ (Akoya Properties) በትልቅ ኃላፊነት መሾማቸውን ይፋ አደረጉ።
አዲሱን የሥራ ኃላፊነት እንዲረከቡ እምነት የጣሉባቸውን አኮያ ፕሮፐርቲስን እና አቶ ሀቢብ ሙሐመድን አመስግነው፣ ይህ አዲስ ምዕራፍ ትልቅ እምነትን፣ ራዕይንና የውጤት ጉዞን ይዞ የመጣ መሆኑን ገልጸዋል።
ኃላፊነታቸውን በተመለከተ ባስተላለፉት መልእክት ባለፉት ዓመታት ያገኟቸው ልምዶች፣ ያለፉባቸው ፈተናዎች፣ የተማሯቸው ትምህርቶች እና አብረዋቸው የሠሩ ሰዎች ሁሉ ለዛሬው ስኬታቸው መሠረት መሆናቸውን አብራርተዋል።
አዲሱ የሥራ ምዕራፍ ትኩረቱን ወደፊት በማድረግ ላይ ያተኮረ መሆኑን የጠቀሱት አቶ ቢንያም፣ በዋናነት ጠንካራ ቡድን በመገንባት፣ ውጤታማ ስትራቴጂዎችን በመቅረፅ እና ዕድሎችን ወደ ተጨባጭ ውጤት በመቀየር ውድድርን የጎላ ሚና የሌለው ማድረግ መሆኗን አብራርተዋል።
በሥራቸውም ለውጤት ከፍተኛ ቁርጠኝነት እና ለመማር ትልቅ ጉጉት እንዳላቸው ገልጸዋል።


















