እጸገነት ይልማ የበሱፍቃድ ሪል እስቴት የብራንድ አምባሳደር ሆና ተመረጠች።
1ሺህ ቤቶችን እየገነባ ያለው በሱፍቃድ ሪል እስቴት ጋዜጠኛ እጸገነት ይልማን አምባሳደር አድርጎ ሾሟል።
ከተመሰረተ ሁለት አመታት ያስቆጠረው ሪል እስቴት ተቋሙ ለሚቀጥሉት ሁለት አመታት በሚቆይ ስምምነት ነው እጸገነት ይልማን አምባሳደር አድርጎ የመረጠው።
በአማራ ክልል ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አረርቲ ከተማ እየገነባ ያለው በሱፍቃድ ሪል እስቴት የቤት ፈላጊዎችን ምርጫ ያሟላና ዘመናዊ መንደር እየፈጠረ የሚገኝ ተቋም መሆኑ ተነግሯል።

በምንጃር ሸንኮራ አረርቲ ከተማ በ230 ሺህ ካሬ ሜትር ላይ እየገነባ ያለው ግዙፍ የመኖርያ መንደር 1ሺህ ቤቶችን እየገነባ እንደሚገኝ አስታውቋል።
ሪል እስቴት ተቋሙ አዲስ አበባን ከደብረብርሀን ጋር በልማት ለማስተሳሰር እንዲሁም የኢንቨስትመንት ፍሰቱን ለማሳደግ በማሰብ ነው ጋዜጠኛ እጸገነት ይልማን አምባሳደር አድርጎ የመረጠው ተብሏል።
እንዲሁም አለም አቀፍ ተደራሽነቱን ለማስፋት በማሰብ እና ከኢትዮጵያ ደንበኞች በተጨማሪም በሰሜን አሜሪካና ካናዳ እንዲሁም እንግሊዝና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በስፋት እንዲቀሳቀስ ያመቸው ዘንድ እጸገነት ይልማን አምባሳደር አድርጎ የመረጠው።


















