ዴማ ሆፕ ሪል እስቴት (Dema Hope Real Estate) ታዋቂዋን የፋሽን ሞዴል ሄላራ ተስፋዬን አምባሳደሩ አድርጎ መሾሙን አስታወቀ
በጥራት፣ በታማኝነት፣ በዘመናዊ የስነ-ሕንጻ ጥበብ (Architectural Elegance) እና የላቀ የእጅ ጥበብ የተገነቡ ምቹ የመኖሪያ ቤቶችን ለደንበኞቹ በማቅረብ የሚታወቀው ተቋሙ፣ ከሄላራ ተስፋዬ ጋር በመሆን በዘርፉ አዳዲስ ስኬቶችን ለማስመዝገብና የቅንጦት አኗኗር ደረጃዎችን (Modern Luxury Living) ከፍ ለማድረግ በትብብር እንደሚሰራ ገልጿል።
ዴማ ሆፕ ሪል እስቴት ስለ አጋርነቱ ባወጣው መግለጫ፣ ድርጅቱ ከመኖሪያ ቦታዎች ግንባታ ባለፈ ዘመናዊ የአኗኗር ዘይቤዎችንና የተሟሉ ማህበረሰቦችን የመቅረጽ ራዕይ ይዞ እየሰራ እንደሚገኝ ጠቁሟል።
ተቋሙ “እያንዳንዱ እንቅስቃሴያችን በዓላማ የሚመራ ነው” በሚል መሪ ቃል፣ በሪል እስቴቱ ዘርፍ የላቀ አገልግሎትና ደረጃቸውን የጠበቁ ቤቶችን ለደንበኞቹ ማቅረቡን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጧል።

















