የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ 3ኛ ዓመት 11ኛ መደበኛ ስብሰባ በ3 ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል። ከውሳኔዎቹ አንዱ ግንባታዎችን የሚመለከት ነው።
በዚህም የከተማዋን ስታንዳርድ እና መዋቅራዊ ፕላን ለማስጠበቅ እንዲሁም መልሶ ማፍረስ እንዳይገጥም ፤ ግንባታዎች ከመንገድ ያላቸው ርቀት ከዚህ በኋላ ወጥነት ያለው የከተማ አሰራር አንዲኖር በማሰብ ከመንገድ መራቅ ያለባቸውን 3 ደረጃዎች ወጥተዋል።
ከአሁን በኋላ የሚገነቡ ማንኛውም ግንባታዎች ፦
- ከዋና ከመንገድ በ10 ሜትር ርቀት መሆን እንደሚገባው ፤
- ከንዑስ ዋና መንገድ 5 ሜትር ርቀት፤
- ሰብሳቢ መንገድ ደግሞ 3 ሜትር ርቀት
በተጨማሪ የውስጥ ለውስጥ መንገድ 2 ሜትር ርቀት መጠበቅ እንዳለባቸው ካቢኔው ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።

















