ኦቪድ ሪል እስቴት (OVID Real Estate) የድርጅቱን ስኬቶች፣ የሰራተኞቹን ታሪክ እና የውስጥ ዜናዎችን የሚያጋራበት «ኦቪድ ታይምስ» (OVID Times) የተሰኘ ወርሃዊ ጋዜጣ በይፋ ማስጀመሩን ገለጸ።
ኩባንያው ይፋ ባደረገው መረጃ መሠረት፣ ጋዜጣው ከአንድ መደበኛ ጋዜጣ በላይ በመሆን በድርጅቱ ውስጥ የሚገኙና ያልተነገረላቸውን «ያልተዘመሩ ጀግኖች» (Unsung Heroes) ታሪክ ለማንሳት፣ የድርጅታችንን ዜናዎችና ስኬቶች ለማጋራት እንዲሁም በቡድኖቻችን መካከል ትብብርን ለማጠናከር የተፈጠረ መድረክ እንደሆነ ተገልጿል።
በጋዜጣው መክፈቻ መርሃ ግብር ላይ የመጀመሪያው «ያልተዘመረለት ጀግና» በመባል የተመረጡት አቶ መሐመድ ሁሴን የራሡን ታሪክ ያካተተውን የመጀመሪያ እትም በክብር መረከቡ ተገልጿል። ይህም ታሪክ ከማንኛውም ትልቅ ስኬት ጀርባ ትጋት፣ ታማኝነት እና ጽናት እንዳለ የሚያሳይ መሆኑን ኩባንያው አመልክቷል።


ኦቪድ ሪል እስቴት የታዋቂውን ፈላስፋ አርስቶትል “The whole is greater than the sum of its parts.” የሚለውን አባባል በመጥቀስ፣ እያንዳንዱ ስኬት የቡድን ሥራ ውጤት መሆኑን እና የእያንዳንዱ ክፍል ሰራተኛ ታሪክ ሊነገርለት እንደሚገባ ገልጿል።
ወደፊትም በየወሩ በሚወጣው በዚህ ጋዜጣ ተጨማሪ ሰራተኞችን እንደሚያከብር፣ አነቃቂ ታሪኮችን እና የድርጅቱን ዋና ዋና ስኬቶች ለህዝብ እንደሚያቀርብ ኩባንያው ጨምሮ አስታውቋል።
ምንጭ: ኦቪድ ሪል እስቴት


















