ካፒታል ሃላፊነቱ የተወሰነ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበር ከኦቪድ ቤቶች ባንክ እና ኦቪድ ሪል እስቴት ጋር በጋራ ለመስራት ተስማማ።
ካፒታል ሃላፊነቱ የተወሰነ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበር ከኦቪድ ቤቶች ባንክ እና ኦቪድ ሪል እስቴት ጋር በአጋርነት ለመስራት በዛሬው እለት የሁለትዮሽ የአጋርነት ስምምነት የፊርማ ስነ-ስርዓት አከናውኗል።

በስምምነት ስነስርዓቱ ላይ እንደተገለጸው ካፒታል ሃላፊነቱ የተወሰነ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበር የገንዘብ እጥረት ችግርን ለመፍታት፣ አሰራሩን ዘመኑን በዋጀ ቴክኖሎጂ ለማዘመን፣ የላቀ የፋይናንስ መረጋጋትን ለማምጣት እንዲሁም አባላት በረጅም ጊዜ ሼር ገዝተው የትርፍ ተጠቃሚ የሚሆኑበት እና የኢንቨስትመንት አቅማቸዉን የሚያጎለብቱበት በአደረጀጀቱ ልዩ ከሆነው የቤት ብድር በረጅም ጊዜ በሰፊው ለማቅረብ በመደራጅት ላይ ከሚገኘው ኦቪድ ቤቶች ባንክ ጋር እዲሁም የአባላቱን የመኖሪያ ቤት ችግር በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ እና የአባሉን ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ከኦቪድ ሪል እስቴት ጋር በአጋርነት ለመስራት የሁለትዮሽ የአጋርነት ስምምነት ዉል ተፈራርሟል።

ከዚህ ጋር ተያይዞ ህብረት ስራ ማህበራት ለንግድ ፤ ለመኪና እና ለቤት የብድር አቅርቦት የፋይናንስ እጥረትን ለመፍታት ከፋይናንስ ተቋማት እና አጋዥ ባለድርሻ አካልት ጋር ትስስር በመፍጠር የአባሎቻቸዉን የብድር አቅርቦት ችግር እንደሚፈቱ ተገልጿል።
ካፒታል ሃላፊነቱ የተወሰነ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበር በህብረት ስራ ማደራጃ አዋጅ ቁጥር 985/2009 አንቀጽ 10 መሰረት ከአዲስ አበባ ከተማ ህብረት ሰራ ኮሚሽን ህጋዊ ፈቃድ ያገኘ እና ለአባላቱ የፋይናንስ አገልግሎቱን አካታች ባደረገ መልኩ ወለድ አልባ እና መደበኛ የቁጠባና የብድር አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝ ህብረት ስራ ማህበር ነው፡፡















