በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የቤት ፋይናንስ አቅራቢ ሆኖ የተቋቋመው ‘’ጎህ ቤቶች ባንክ’’ በ2015 የበጀት ዓመት ያልተጣራ 6.38 ሚሊዮን ብር ማትረፉን ተናገረ።
ትርፉ በ2014 የበጀት ዓመት ከተገኘው ትርፍ ጋር ሲነፃፀር የ19 በመቶ ቅናሽ አሳይቷል ተብሏል የጎህ ቤቶች ባንክ የባለአክሲዮኖች 2ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔው በዛሬው እለት በተካሄደበት ወቅት።
በበጀት ዓመቱ የተሰበሰበው ተቀማጭ ገንዘብ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ255.3 በመቶ አድጓል ተብሏል፡፡ አጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘብ 911.8 ሚሊዮን ብር ደርሷል ተብሏል። ሸገር ኤፍኤም














