ፓልም ሪል እስቴት ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ለመቄዶኒያ የአዕምሮ ህሙማን መርጃ የ 27 ሚሊየን ብር ቤት ድጋፍ አደረገ።
ተቋሙ በገርጂ መብራት ሀይል ሳይት ካሉ አፓርትመንት ቤቶች አንድ ባለ 177 ካሬ ሜትር ባለ ሶስት መኝታ ድጋፍ ማድረጉ ነው የተገለፀው።
የፓልም ሪል እስቴት ዋና ስራ አስፈጻሚ ሰላማዊት አያሌው “ተቋማችን ከሪል እስቴት ልማት ጎን ለጎን ማህበራዊ ሃላፊነትን ለመወጣት በማለም ስጦታውን ለማድረግ ወስኗል” ብለዋል።
የመቄዶኒያ መስራች አቶ ቢንያም በበኩላቸው የፓልም ሪል እስቴት ላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
ሌሎች በሪል እስቴትና መሰል ዘርፎች የተሰማሩ አካላት የፓልም ሪል እስቴትን ፈለግ በመከተል ማዕከሉን እንዲደግፉ ጥሪ አቅርበዋል።
ማዕከሉ ከ 7 ሺህ 50 ዐ በላይ የአዕምሮ ህሙማንንና አረጋውያንን በ 25 ከተሞች በሚገኙ ማዕከላቱ ተረጂዎችን የመንከባብ ስራዎችን እየሰራ ሲሆን አሁንም ቀጣይነት ያለው ድጋፍ እንደሚያስፈልገው ተገልጿል።


















